ንቁ! ጥቅምት 2012
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
በትምህርት ስኬታማ መሆን የሚቻለው እንዴት ነው?
ከትምህርት ይበልጥ ጥቅም ማግኘት ትችላለህ። በእነዚህ ተከታታይ ርዕሶች ላይ በትምህርትህ ስኬታማ ለመሆን የሚረዱህ አምስት ቁልፍ ነጥቦችን እንመለከታለን።
የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ
የተደራጀህ ሁን
ይህ ርዕስ ከቤት ሥራ ጋር በተያያዘ የሚፈጠረውን ውጥረት ለመቀነስና በትምህርት ጥሩ ውጤት ለማምጣት የሚረዱ ነጥቦችን ይዟል።
ከመጠን ባለፈ ውፍረት የሚሠቃዩ ወጣቶች ምን መፍትሔ አላቸው?
በፍጥነት የሚዘጋጁ ለጤና ጠቃሚ ያልሆኑ ምግቦችን የማግበስበስ ልማድ የነበረው አንድ ወጣት ቀላል ማስተካከያዎችን በማድረግ የአመጋገብ ልማዱን እንዴት እንደተቆጣጠረ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
የቆላ ጎሪላዎችን መጎብኘት
ዛንጋ እንዶኪ ወደተባለ ብሔራዊ ፓርክ አብራችሁን በመሄድ በምዕራባዊ ቆላማ አካባቢ የሚኖረውን ማኩምባ የተባለ ጎሪላ እንድትጎበኙ እንጋብዛችኋለን
የወጣቶች ጥያቄ
ከትዳር ምን መጠበቅ እችላለሁ?—ክፍል 2
በትዳር ውስጥ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ያልተጠበቁ ተፈታታኝ ሁኔታዎችን ለመወጣት ራስህን እንዴት ማዘጋጀት እንደምትችል ለማወቅ ይህን ርዕስ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።
የሚያስጨንቁ የዜና ዘገባዎችና ልጆቻችሁ
የዜና ዘገባዎች በልጆቻችሁ ላይ ፍርሃት ያሳድራሉ? እነዚህ ዘገባዎች በልጆቻችሁ ላይ ተጽዕኖ እንዳያሳድሩ ልትረዷቸው የምትችሉት እንዴት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
ከዋክብት በሕይወትህ ላይ ተጽዕኖ ያሳድራሉ?
ብዙ ሰዎች፣ ሕይወታቸውን ለመምራት የሚያስችል ሐሳብና ምክር ለማግኘት ወደ ኮከብ ቆጠራ ዘወር ይላሉ። ለመሆኑ ከዋክብት ሊረዱን ይችላሉ?
የወላጅነት ኃላፊነትህን በሚገባ መወጣት
በዛሬው ጊዜ ልጆቻችሁ የሚደቀኑባቸውን የሥነ ምግባር ፈተናዎች መቋቋም እንዲችሉ ልትረዷቸው የምትችሉት እንዴት ነው?
መጽሐፍ ቅዱስ—ትክክለኛ ትንቢት የያዘ መጽሐፍ—ክፍል—6
በዛሬው ጊዜ በዓለም ላይ የሚታዩት ሁኔታዎች የሚያመለክቱት ነገር አለ? ያለንበት ዘመን የተለየ መሆኑን የሚጠቁሙ ሰባት ትንቢቶችን እንድትመረምር እንጋብዝሃለን።
ከዓለም አካባቢ
የተካተቱት ዜናዎች፦ የከተማ ኑሮ የሚፈጥረው ውጥረት፣ ፌስቡክ እንዲሁም ቴሌቪዥን የመመልከት ልማድ በዕድሜያችን ላይ የሚያሳድሩት ተጽዕኖ።
ቤተሰብ የሚወያይበት
በዚህ ወር ስለ ኖኅ፣ ስለ ነህምያ እንዲሁም በዛምቢያ ስላሉ የይሖዋ ምሥክሮች ማወቅ ትችላለህ።