በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአርማጌዶን ጦርነት የሚደረገው የት ነው?

የአርማጌዶን ጦርነት የሚደረገው የት ነው?

አንባቢያን የሚያነሱት ጥያቄ

የአርማጌዶን ጦርነት የሚደረገው የት ነው?

የአርማጌዶን ጦርነት በአንድ የተወሰነ የጦር ሜዳ ላይ የሚካሄድ አይደለም። ከዚህ ይልቅ በመላው ምድር ላይ የሚደረግ ጦርነት ነው። እንዲህ የምንለው ለምንድን ነው? ምክንያቱም በጦርነቱ የሚካፈሉት የሁለቱ ተጻራሪ ቡድኖች አባላት እጅግ ብዙ ከመሆናቸው የተነሳ እነሱን የሚይዝ አንድ የተወሰነ ስፍራ ሊኖር አይችልም።

አርማጌዶን ወይም ሃር ማጌዶን ‘ሁሉን የሚችል አምላክ ታላቅ የጦርነት ቀን’ ተብሎም ይጠራል። ይሖዋ አምላክ፣ ከክፉዎቹ የምድር ነገሥታት ጋር እንዲዋጉ የመላእክት ሠራዊትን ለመሰብሰብ ልጁን ኢየሱስ ክርስቶስን ይጠቀማል።—ራእይ 16:14፤ 19:11-16

ብሔራት፣ በሰይጣን ኃይሎች ተደልለው ወደ ጦርነቱ ይገባሉ። መጽሐፍ ቅዱስ ‘የዓለም ነገሥታት በሙሉ በአጋንንት መናፍስት [እየተነዱ]፣ በዕብራይስጥ አርማጌዶን በሚባል ስፍራ’ እንደሚሰበሰቡ ይናገራል።—ራእይ 16:14-16

የመጽሐፍ ቅዱስ አንባቢዎችን ትኩረት በመሳብ ረገድ ከቅዱሳን መጻሕፍት መካከል የራእይ መጽሐፍን የሚተካከለው የለም። በራእይ መጽሐፍ ላይ የሰፈረው ሐሳብ ቃል በቃል መወሰድ አለበት ብለው የሚያምኑ በርካታ ሰዎች ጦርነቱ ይካሄድበታል ብለው የሚያስቡትን ቦታ ለይተው የሚጠቅሱ ሲሆን በዚያ አካባቢ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ሁሉ በፍርሃት ስሜት ይከታተላሉ። የአርማጌዶን ጦርነት የሚካሄደው በተወሰነ ቦታ ነው የሚለው አመለካከት ኦኮሜንየስ የተባለ አንድ ግሪካዊ ጸሐፊ በስድስተኛው መቶ ዘመን ከክርስቶስ ልደት በፊት ስለ ራእይ መጽሐፍ ባሰፈረው ጥንታዊ ዘገባ ላይም ይገኛል።

በዳላስ የሚገኝ የአንድ ሃይማኖታዊ የትምህርት ተቋም ፕሬዚዳንት የነበሩ ጆን ዋልቮርድ የተባሉ ሰው፣ አጥባቂ በሆኑ ቀሳውስት ዘንድ በሰፊው ተቀባይነት ያለውን ሐሳብ በመደገፍ እንዲህ ብለዋል:- አርማጌዶን “ተስፋው የጨለመበት ይህ ዓለም በመካከለኛው ምሥራቅ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚያደርገው ከንቱ ጦርነት ነው።” ዋልቮርድ ይህ ታላቅ ጦርነት የሚደረገው “‘በመጊዶ ተራራ’ ላይ ሲሆን ይህ ቦታ በሰሜናዊ ፍልስጥኤም በሚገኝ ትልቅ ሸለቆ መጨረሻ ላይ ያለ ጉብታ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ይሁን እንጂ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ የሰፈረው ሐሳብ አርማጌዶን የሚባለውን ቦታ ቃል በቃል ለማመልከት ታስቦ የተጻፈ አይደለም። መጽሐፉ በመክፈቻው ላይ እንደሚናገረው ዘገባው የቀረበው ‘በምልክቶች’ አማካኝነት ነው። (ራእይ 1:1 NW) ከረጅም ጊዜ በፊት የይሖዋ ምሥክሮች የቅዱሳን ጽሑፎች ጥናት (እንግሊዝኛ) በተባለው መጽሐፋቸው ጥራዝ 4 ላይ “ቃል በቃል በመጊዶ ኮረብታማ ቦታ ላይ ሰዎች ይሰበሰባሉ ብለን አንጠብቅም” ብለዋል።

የመጊዶ ታሪክ የአምላክ ጠላቶች ከጥፋት ሊያመልጡ እንደማይችሉ ያሳያል። በመሆኑም፣ አምላክ በአርማጌዶን ጦርነት አማካኝነት ማንኛውንም ዓይነት የሥነ ምግባር ውድቀትና ክፋት ከመላው ምድር ላይ ያስወግዳል።—ራእይ 21:8

ይሖዋ አምላክንና ልጁ ኢየሱስ ክርስቶስን የሚወዱ ሁሉ አርማጌዶንን የሚፈሩበት ምንም ምክንያት የለም። አምላክ በዚህ ጦርነት የሚያጠፋው ከስህተታቸው ለመታረም ፈቃደኛ ያልሆኑ ክፉ ሰዎችን ብቻ ነው። ጦርነቱ ሰዎችን ሁሉ በጅምላ የሚያጠፋ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ፣ ይሖዋ ‘በእውነት እያመለኩት የሚኖሩትን እንዴት እንደሚያድናቸው ያውቃል’ በማለት ይናገራል። (2 ጴጥሮስ 2:9) በመዝሙር 37:34 ላይ የሚገኘው አስደሳች ተስፋ እንዲህ ይላል:- “እግዚአብሔርን [“ይሖዋን፣” NW] ደጅ ጥና፤ መንገዱንም ጠብቅ፤ ምድሪቱን ትወርስ ዘንድ ከፍ ከፍ ያደርግሃል፤ ክፉዎችም ሲጠፉ ታያለህ።”