በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

 የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | መጸለይ እንዳለብህ ይሰማሃል?

ሰዎች የሚጸልዩት ለምንድን ነው?

ሰዎች የሚጸልዩት ለምንድን ነው?

የመጸለይ ልማድ አለህ? ብዙ ሰዎች የመጸለይ ልማድ አላቸው፤ በአምላክ የማያምኑ አንዳንድ ሰዎችም እንኳ የሚጸልዩበት ጊዜ አለ። ይሁን እንጂ ሰዎች የሚጸልዩት ለምንድን ነው? በፈረንሳይ የተደረገ አንድ ጥናት እንዳመለከተው ከሆነ ግማሽ የሚሆኑት የአገሪቱ ዜጎች የሚጸልዩት ወይም የሚያሰላስሉት “ጥሩ ስሜት እንዲሰማቸው ብቻ” ነው። እንደ አብዛኞቹ አውሮፓውያን ሁሉ እነዚህ ሰዎችም የሚጸልዩት ሃይማኖታዊ ግዴታ ለመፈጸም ብለው አይደለም። ከዚህ ይልቅ “በመጸለይ የሚመጣውን የመረጋጋት ስሜት” ማግኘት ስለሚፈልጉ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ አንዳንድ አማኞች ወደ አምላክ ዘወር የሚሉት ሲቸግራቸው ብቻ ነው፤ በዚህ ጊዜ አፋጣኝ መልስ ለማግኘት ይጠብቃሉ።—ኢሳይያስ 26:16

አንተስ ስለ ጸሎት ምን ይሰማሃል? ጸሎትን የምትመለከተው ተረጋግተህ እንድታስብ የሚረዳህ ነገር እንደሆነ ብቻ አድርገህ ነው? በአምላክ የምታምን ከሆነ ደግሞ ጸሎት ጠቃሚ መሆኑን በራስህ ሕይወትህ ተመልክተሃል? ወይስ ጸሎትህ መልስ ሳያገኝ እንደቀረ ይሰማሃል? መጽሐፍ ቅዱስ ጸሎት ጥሩ ስሜት እንዲሰማህ ከማድረግ ባለፈ ወደ አምላክ ለመቅረብ የሚረዳህ ልዩ መንገድ መሆኑን እንድትገነዘብ ይረዳሃል።