በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ዓለም በሙሉ በአንድ መንግሥት የሚተዳደርበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

ዓለም በአንድ መንግሥት ብቻ በሚተዳደርበት ወቅት የዓለም ሕዝብ አንድነት የሚኖረው እንዴት ነው? ኢሳይያስ 32:1, 17፤ 54:13

ዓለም በአንድ መንግሥት ቢተዳደር የሰው ልጆች ምን ያህል ሊጠቀሙ እንደሚችሉ እስቲ አስበው። በዛሬው ጊዜ ብዙዎች በከፋ ድህነት ሲማቅቁ አንዳንዶች ግን ከልክ በላይ ሀብታም ናቸው። ዓለም በሙሉ የሚተዳደረው በአንድ ጥሩ መንግሥት ቢሆን ኖሮ የዓለም ሕዝብ በሙሉ የሚያስፈልገውን ነገር በበቂ መጠን ማግኘት ይችል ነበር። ታዲያ የሰው ልጆች እንዲህ ያለ መንግሥት ማቋቋም የሚችሉ ይመስልሃል?—ኤርምያስ 10:23ን አንብብ።

ባለፉት ዘመናት፣ መንግሥታት የተገዢዎቻቸውን በተለይም የድሆችን ፍላጎት ማሟላት ሳይችሉ ቀርተዋል። እንዲያውም አንዳንድ መንግሥታት ሕዝባቸውን ይጨቁናሉ። (መክብብ 4:1፤ 8:9) ይሁንና ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በዓለም ላይ ያሉትን መንግሥታት በሙሉ የሚተካ አንድ መንግሥት እንደሚያቋቁም ቃል ገብቷል። የዚህ መንግሥት ንጉሥ ተገዢዎቹ የሚያስፈልጓቸውን ነገሮች በሙሉ ያሟላል።—ኢሳይያስ 11:4ን እና ዳንኤል 2:44ን አንብብ።

የአምላክ መንግሥት ምን ያከናውናል?

ይሖዋ አምላክ ከሁሉ የተሻለውን ገዢ ማለትም ልጁን ኢየሱስን የዚህ መንግሥት ንጉሥ አድርጎ ሾሞታል። (ሉቃስ 1:31-33) ኢየሱስ ምድር ላይ በነበረበት ወቅት ሰዎችን መርዳት ያስደስተው ነበር። ወደፊት ንጉሥ ሲሆን ደግሞ የዓለምን ሕዝብ በሙሉ የሚገዛ ሲሆን መከራን ያስወግዳል።—መዝሙር 72:8, 12-14ን አንብብ።

ሁሉም ሰዎች ኢየሱስን ንጉሣቸው አድርገው ይቀበሉታል? በፍጹም። ያም ሆኖ ይሖዋ ትዕግሥተኛ ነው። (2 ጴጥሮስ 3:9) ሰዎች ኢየሱስን ገዢያቸው አድርገው እንዲቀበሉት አጋጣሚ እየሰጣቸው ነው። በቅርቡ ግን ኢየሱስ ክፉ ሰዎችን ከምድር ላይ የሚያጠፋ ሲሆን ሰላምና ደኅንነት እንዲሰፍን ያደርጋል።—ሚክያስ 4:3, 4ን አንብብ።