በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 127

ምን ዓይነት ሰው መሆን አለብኝ?

ምን ዓይነት ሰው መሆን አለብኝ?

(2 ጴጥሮስ 3:11)

  1. 1. ይሖዋ አምላኬ፣ እንዴት ልክፈልህ?

    ለሰጠኸኝ ሕይወት በምን ላመስግንህ?

    ቃልህ መስታወት ነው ውስጤን የማይበት፤

    እርዳኝ ልመልከት ራሴን በሐቀኝነት።

    (መሸጋገሪያ)

    አንተን ለማገልገል ገብቻለሁ ቃል፤

    የማደርገው ሁሉ አይደለም ለይምሰል።

    ሙሉ ልቤን ላንተ እሰጥሃለሁ፤

    አንተን ማስደሰት እፈልጋለሁ።

    ልመርምረው ውስጤን ልወቀው ልቤን፤

    የምትፈልገውን ዓይነት ሰው መሆኔን።

    ታማኞችህን ሁሌ ትባርካለህ፤

    እኔም እንደ ወዳጆችህ ላስደስትህ።

(በተጨማሪም መዝ. 18:25⁠፤ 116:12⁠ን እና ምሳሌ 11:20⁠ን ተመልከት።)