በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 129

ጸንተን እንጠብቃለን

ጸንተን እንጠብቃለን

(ማቴዎስ 24:13)

  1. 1. በፈተና ወቅት

    ክርስቶስ መጽናት የቻለው፣

    የሚያገኘውን

    ሽልማት በማሰቡ ነው።

    በተስፋው ላይ ነበር

    ትኩረቱ ያረፈው።

    (አዝማች)

    መጽናት ያስፈልገናል፤

    መቆም በ’ምነታችን።

    ፍቅሩ ዋስትናችን ነው፤

    ጸንቶ መኖር ነው ሁሌም ግባችን።

  2. 2. ችግር፣ መከራ

    ለጊዜው ይደርስብናል።

    አሁን ብናዝንም

    ይታየናል ብሩሕ ተስፋ።

    ያ ጊዜ ’ስኪመጣ

    ወደፊት እንግፋ።

    (አዝማች)

    መጽናት ያስፈልገናል፤

    መቆም በ’ምነታችን።

    ፍቅሩ ዋስትናችን ነው፤

    ጸንቶ መኖር ነው ሁሌም ግባችን።

  3. 3. ተስፋ አንቆርጥም፤

    በውስጣችን ፍርሃት የለም።

    ታማኞች እንሁን፣

    ስንጠብቅ የአምላክን ቀን።

    በእምነት እንጽና፤

    ጊዜው በጣም ቀርቧል።

    (አዝማች)

    መጽናት ያስፈልገናል፤

    መቆም በ’ምነታችን።

    ፍቅሩ ዋስትናችን ነው፤

    ጸንቶ መኖር ነው ሁሌም ግባችን።

(በተጨማሪም ሥራ 20:19, 20⁠ን፣ ያዕ. 1:12⁠ን እና 1 ጴጥ. 4:12-14⁠ን ተመልከት።)