በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 20

ውድ ልጅህን ሰጠኸን

ውድ ልጅህን ሰጠኸን

(1 ዮሐንስ 4:9)

  1. 1. ይሖዋ፣ ውድ አባት፣

    ያለተስፋ ነበርን፤

    አሁን ግን በቤዛው

    ተስፋ አገኘን!

    አንሳሳም ለመስጠት፣

    ላንተ ምርጣችንን።

    እንናገራለን

    ታላቅ ውለታህን።

    (አዝማች)

    ተወዳጅ ልጅህን

    ለኛ ሰጥተኸናል፤

    ከልብ እንዘምርልህ፤

    ይገባሃልና ክብር።

  2. 2. ወዳንተ ስቦናል

    ደግነት፣ ምሕረትህ።

    ስምህን ነገርከን፤

    ወዳጃችን ሆንክ።

    ግን ታላቅ ስጦታህ፣

    ከሁሉም ’ሚበልጠው፣

    እኛ እንድንኖር

    ልጅህ መሞቱ ነው።

    (አዝማች)

    ተወዳጅ ልጅህን

    ለኛ ሰጥተኸናል፤

    ከልብ እንዘምርልህ፤

    ይገባሃልና ክብር።

    (መጨረሻ)

    ይሖዋ፣ ውድ አባት፣ ምስጋና ይድረስህ።

    ልጅህን ሰጠኸን፤ ከልብ እናመስግንህ።

(በተጨማሪም ዮሐ. 3:16⁠ን እና 15:13⁠ን ተመልከት።)