መዝሙር 28
የይሖዋ ወዳጅ መሆን
(መዝሙር 15)
-
1. ያንተ ወዳጅ ማን ነው?
በድንኳንህ ’ሚያድረው?
በደንብ የሚያውቅህ፣ የምታምነው፣
ያንተ ወዳጅ ማን ነው?
ቃልህን የሚወድ፣
የሚታመንብህ፣
ጥሩና ታማኝ የሆነ ሰው፣
ሕይወቱን ’ሚሰጥህ።
-
2. ያንተ ወዳጅ ማን ነው?
ዙፋንህ ’ሚቀርበው?
ደስ የምትሰኝበትና
በስም የምታውቀው?
ስምህን ’ሚያወድስ፣
ቃልህን ’ሚጠብቅ፣
ሁሌም ሐቀኛ የሆነ ሰው፣
ከመዋሸት ’ሚርቅ።
-
3. የሚያስጨንቀንን
በጸሎት ስንነግርህ፣
’ሚያስፈልገንን ታሟላለህ፤
ስቦናል ይህ ፍቅርህ።
ሁሌም ያንተ ወዳጅ
መሆን ያጓጓናል፤
ከዚህ የሚበልጥ ወዳጅነት
ከወዴት ይገኛል?
(በተጨማሪም መዝ. 139:1ን እና 1 ጴጥ. 5:6, 7ን ተመልከት።)