በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 66

ምሥራቹን አውጁ

ምሥራቹን አውጁ

(ራእይ 14:6, 7)

  1. 1. ሚስጥር የነበረው የመንግሥቱ እውነት፣

    አሁን ታወቀ የተስፋው ዘር ማንነት።

    አምላክ ጽድቅን በመውደዱ፣ በምሕረቱ፣

    አሰበ ሰውን ለማንጻት ከኃጢያቱ።

    ወሰነ ምድርን ሊያስተዳድር በልጁ፤

    እሱ ባሰበው ቀን

    እንዲወለድ መንግሥቱ።

    ለሚወደው ልጁ ሊያዘጋጅ ሙሽራ፣

    ታናሹን መንጋ ወደ መንግሥቱ ጠራ።

  2. 2. ምሥራቹ ከጥንትም ነው ’ሚታወቀው፤

    ይሖዋ ይፈልጋል እንድናውጀው።

    መላእክቱም ከኛ ጋር ይሰማራሉ፤

    መንግሥቱን ስናውጅ እኛን ይረዳሉ።

    ስሙን የሚያስቀድስ ሥራ ተሰጥቶናል፤

    ይህን ኃላፊነት በመስጠት

    አክብሮናል።

    የዘላለሙን ምሥራች መስበካችን፣

    ክብር ነው የሱ ምሥክር መሆናችን።

(በተጨማሪም ማር. 4:11⁠ን፣ ሥራ 5:31⁠ን እና 1 ቆሮ. 2:1, 7⁠ን ተመልከት።)