በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘ሰላሜ እንደ ወንዝ’

‘ሰላሜ እንደ ወንዝ’

አውርድ፦

  1. 1. ዘንድሮስ ባሰበት ያለም ጣጣ፤

    ሐሳብ፣ ጭንቀቱ የማይሰጥ ፋታ።

    ሸክምህን ስጠኝ ያለኝ እሱ፤

    ይሰማኛል፤ ፈጣን ነው መልሱ።

    (አዝማች)

    ሰላም ሰጠኝ የሚፈውስ፤

    ልብ የሚያርስ፣ እንደ ወንዝ።

    ብርታት፣ አቅም ሰጥቶ፤

    በተስፋው አጽንቶ፤ “አይዞህ!” አለኝ ደግፎ።

    ሰላሜ በዛ እንደ ወንዝ፣ ዘላለም ላይቀንስ!

  2. 2. ጭንቀቴን ከሱ አልከልልም፤

    ይሰማል ምልጃዬን፤ ችላ አይልም።

    በታማኝ ፍቅሩ አቅፎ፣ ደግፎ

    አረጋጋኝ ጎኔ ቆሞ።

    (አዝማች)

    ሰላም ሰጠኝ የሚፈውስ፤

    ልብ የሚያርስ፣ እንደ ወንዝ።

    ብርታት፣ አቅም ሰጥቶ፤

    በተስፋው አጽንቶ፤ “አይዞህ!” አለኝ ደግፎ።

    ሰላሜ በዛ እንደ ወንዝ፣ ዘላለም ላይቀንስ!

    (አዝማች)

    ሰላም ሰጠኝ የሚፈውስ፤

    ልብ የሚያርስ፣ እንደ ወንዝ።

    ብርታት፣ አቅም ሰጥቶ፤

    በተስፋው አጽንቶ፤ “አይዞህ!” አለኝ ደግፎ።

    ሰላሜ በዛ እንደ ወንዝ፣ ዘላለም ላይቀንስ!