በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሰኔ 28, 2021
ሕንድ

በላቲን ፊደላት የተዘጋጀው የታሚል ቋንቋ አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ወጣ

በላቲን ፊደላት የተዘጋጀው የታሚል ቋንቋ አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ወጣ

ሕንድ ውስጥ፣ በላቲን ፊደላት የተዘጋጀው የታሚል ቋንቋ አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ ሰኔ 27, 2021 ወጣ። በኢንተርኔት አማካኝነት የተካሄደው ስብሰባ በ16 አገሮች ለሚኖሩ የታሚል ተናጋሪ ወንድሞችና እህቶች ተላልፏል።

አጭር መረጃ

  • በዓለም ዙሪያ ታሚል የሚናገሩ 85 ሚሊዮን ሰዎች እንዳሉ ይገመታል

  • ታሚል በሚጠቀሙ 334 ጉባኤዎች እና 32 ቡድኖች ውስጥ የሚያገለግሉ ከ20,500 የሚበልጡ አስፋፊዎች አሉ

  • በሥራው የተካፈሉት 5 ተርጓሚዎች ሥራውን ለማጠናቀቅ 6 ወር ፈጅቶባቸዋል

በታሚል ፊደላት የተዘጋጀው አዲስ ዓለም ትርጉም የወጣው መስከረም 2016 ነበር። ይህ መጽሐፍ ቅዱስ በመላው ዓለም ለሚገኙት ታሚል ተናጋሪዎች ትልቅ ጥቅም አስገኝቷል። ሆኖም አንዳንድ ታሚል ተናጋሪዎች የታሚል ፊደላትን ማንበብ ስለሚከብዳቸው የላቲን ፊደላትን ማንበብ ይመርጣሉ።

አንዲት ተርጓሚ ስለ ግል ጥናቷ ስትናገር እንዲህ ብላለች፦ “የታሚል ፊደላትን ማንበብ ስለሚከብደኝ የምጠቀመው የእንግሊዝኛውን መጽሐፍ ቅዱስ ነበር። አዲሱ እትም በጣም ይጠቅመኛል።”

ይህ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በርካታ ወንድሞችና እህቶች የአምላክን ቃል “በለሆሳስ” እንዲያነቡ እንዲሁም በሕይወታቸውና በአገልግሎታቸው ደስታና ስኬት እንዲያገኙ እንደሚረዳቸው እርግጠኞች ነን።—ኢያሱ 1:8