በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

እስራኤል

ታሪካዊ እመርታዎች በእስራኤል

ታሪካዊ እመርታዎች በእስራኤል
  1. ግንቦት 1, 2015—ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ በራናና ከተማ የይሖዋ ምሥክሮችን በሰላም የመሰብሰብ መብት አስከበረ

    ተጨማሪ መረጃ

  2. የካቲት 5, 2007—በጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ድጋፍ፣ ፍርድ ቤቱ ሃይፋ ኢንተርናሽናል ኮንግረስ ሴንተር የተባለው ድርጅት ሕንፃውን ለይሖዋ ምሥክሮች ለማከራየት ፈቃደኛ ባለመሆን በእነሱ ላይ መድልዎ እንደፈጸመ በየነ

  3. 1990ዎቹ መጨረሻ—የአይሁድ ሃይማኖታዊ ንቅናቄ አራማጆች በይሖዋ ምሥክሮች ላይ የሚፈጽሙትን የኃይል ጥቃትና በደል አፋፋሙ

  4. መስከረም 7, 1992—የአውራጃው ይግባኝ ሰሚ ኮሚሽን የይሖዋ ምሥክሮች በቴል አቪቭ ያለውን የስብሰባ አዳራሻቸውን እንዳይጠቀሙ ያስተላለፈውን ውሳኔ ቀለበሰ፤ ውሳኔውን የለወጠው ጠቅላይ አቃቤ ሕጉ ያወጣውን መግለጫ ተከትሎ ነው

  5. ኅዳር 15, 1963ዎች ታወር ባይብል ኤንድ ትራክት ሶሳይቲ የተባለው የይሖዋ ምሥክሮች ሕጋዊ ተቋም በመንግሥት እውቅና ተሰጥቶት ተመዘገበ

  6. ጥር 1, 1963—የይሖዋ ምሥክሮች በሃይፋ ቅርንጫፍ ቢሮ ከፈቱ፤ በኋላም ቅርንጫፍ ቢሮው ወደ ቴል አቪቭ ተዛወረ

  7. 1920—ብሪታንያ መካከለኛውን ምሥራቅ በሞግዚትነት ታስተዳድር በነበረበት ጊዜ የይሖዋ ምሥክሮች የመጀመሪያውን ጉባኤ አቋቋሙ እንዲሁም ሥራቸውን የሚያስተባብሩበት ቢሮ ከፈቱ