በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በስተግራ፦ በማዊ ደሴት፣ በኪሄይ መንደር የተከሰተው ሰደድ እሳት። በስተቀኝ፦ በማዊ ደሴት፣ ላሃይና አካባቢ ሰደድ እሳቱ ያደረሰው ውድመት

ነሐሴ 11, 2023 | የታደሰው፦ መስከረም 29, 2023
ዩናይትድ ስቴትስ

ወቅታዊ መረጃ—ሰደድ እሳት በአንዳንድ የሃዋይ ደሴቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከተለ

ወቅታዊ መረጃ—ሰደድ እሳት በአንዳንድ የሃዋይ ደሴቶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት አስከተለ

ነሐሴ 8, 2023 ከሃዋይ ደሴቶች መካከል በግዙፍነቷ ሁለተኛ ደረጃ በምትይዘው በማዊ ደሴት ሰደድ እሳት ተከስቷል። ደሴቶቹ በሚገኙበት ውቅያኖስ ላይ የተከሰተው አውሎ ነፋስ፣ ሰደድ እሳቱ በፍጥነት እንዲዛመት አድርጓል። የመገናኛ መሠረተ ልማቶች፣ መኖሪያ ቤቶችና የንግድ ቦታዎች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል። የአካባቢው ባለሥልጣናት፣ በተለያዩ የደሴቲቱ ክፍሎች የሚገኙ ነዋሪዎች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ትእዛዝ አስተላልፈዋል። ቁጥራቸው ከ97 ያላነሰ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ ተረጋግጧል። የእሳት አደጋ ሠራተኞች፣ “ትልቁ ደሴት” ተብሎ በሚጠራው የሃዋይ ደሴት ላይም አነስተኛ ሰደድ እሳቶችን ለማጥፋት እየተረባረቡ ነው።

አደጋው በጀመረበት ጊዜ በአካባቢው የሚኖሩ ወንድሞች የሚከተሉትን መረጃዎች ልከውልናል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • የሚያሳዝነው 1 በዕድሜ የገፋ ወንድም በሰደድ እሳቱ ምክንያት ሕይወቱን አጥቷል

  • 307 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል

  • 42 መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል

  • 2 መኖሪያ ቤቶች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 38 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 1 የስብሰባ አዳራሽ ቀላል ጉዳት ደርሶበታል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው የሚገኙ የጉባኤ ሽማግሌዎች አደጋው በደረሰበት አካባቢ ለሚገኙ ወንድሞችና እህቶች መንፈሳዊና ቁሳዊ እርዳታ እያደረጉ ነው

  • የእርዳታ እንቅስቃሴውን እንዲያስተባብር የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል

የአምላክ መንግሥት በዚህ የመጨረሻ ዘመን ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ጨምሮ በብዙ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ላሉት አውዳሚ የአየር ሁኔታዎች ዘላቂ መፍትሔ የሚሰጥበትን ጊዜ በጉጉት እንጠባበቃለን።—ማርቆስ 4:39