በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ትንቢት ምንድን ነው?

ትንቢት ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 ትንቢት በአምላክ መንፈስ መሪነት የሚነገር መልእክት ሲሆን አምላክ ፈቃዱን ለመግለጥ የሚጠቀምበት መንገድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ነቢያት “ከአምላክ የተቀበሉትን ትንቢት በመንፈስ ቅዱስ ተገፋፍተው” እንደተናገሩ ይገልጻል። (2 ጴጥሮስ 1:20, 21) በመሆኑም ነቢይ፣ የአምላክን መልእክት ተቀብሎ ለሌሎች የሚያስተላልፍ ሰው ነው።—የሐዋርያት ሥራ 3:18

ነቢያት ከአምላክ መልእክት የተቀበሉት እንዴት ነበር?

 አምላክ ሐሳቡን ለነቢያት ለማስተላለፍ በተለያዩ ዘዴዎች ተጠቅሟል፦

  •   በጽሑፍ። አምላክ ይህን ዘዴ ቢያንስ አንድ ጊዜ ይኸውም በጽሑፍ የሰፈሩትን አሥርቱን ትእዛዛት በቀጥታ ለሙሴ በሰጠበት ወቅት ተጠቅሞበታል።—ዘፀአት 31:18

  •   በመላእክት በኩል በመናገር። ለምሳሌ አምላክ፣ ሙሴ ለግብፁ ፈርዖን የሚነገረውን መልእክት ያሳወቀው በአንድ መልአክ አማካኝነት ነው። (ዘፀአት 3:2-4, 10) አምላክ አንድን መልእክት ቃል በቃል መግለጽ ሲፈልግ በመላእክት ይጠቀም ነበር፤ ለሙሴ የሚከተለውን መልእክት በነገረው ጊዜም ያደረገው ይህንኑ ነው፦ “ከአንተም ሆነ ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን የምገባው በእነዚህ ቃላት መሠረት ስለሆነ እነዚህን ቃላት ጻፍ።”—ዘፀአት 34:27 a

  •   በራእይ። ነቢያት ንቁ በሆኑበትና ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን በሚያውቁበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ራእይ ያዩበት ጊዜ አለ። (ኢሳይያስ 1:1፤ ዕንባቆም 1:1) ራእዩ እውን ከመሆኑ የተነሳ ራእዩን የተመለከተው ነቢይ ተሳትፎ ያደረገባቸው ጊዜያት አሉ። (ሉቃስ 9:28-36፤ ራእይ 1:10-17) በሌሎች ጊዜያት ደግሞ ነቢዩ ራእዩን የሚያየው በሰመመን ውስጥ ሆኖ ሊሆን ይችላል። (የሐዋርያት ሥራ 10:10, 11፤ 22:17-21) አምላክ፣ ነቢዩ ተኝቶ ሳለ በሕልም መልእክቱን የገለጠበት ጊዜም ነበር።—ዳንኤል 7:1፤ የሐዋርያት ሥራ 16:9, 10

  •   አስተሳሰብን በመምራት። አምላክ የነቢያቱን አስተሳሰብ በመምራት መልእክቱን አስተላልፏል። “ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው” የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስም ይህን ሐሳብ የሚያስተላልፍ ነው። “በአምላክ መንፈስ መሪነት” የሚለው አገላለጽ “አምላክ የተነፈሰበት” ተብሎም ሊተረጎም ይችላል። (2 ጢሞቴዎስ 3:16 ዚ ኤምፋሳይዝድ ባይብል) አምላክ በአገልጋዮቹ አእምሮ ውስጥ የእሱን ሐሳብ “ለመተንፈስ” ቅዱስ መንፈሱን ወይም ኃይሉን ተጠቅሟል። መልእክቱ የአምላክ ቢሆንም ነቢዩ በራሱ አባባል ይገልጸዋል።—2 ሳሙኤል 23:1, 2

ትንቢት የሚያመለክተው ስለ ወደፊቱ ጊዜ የተነገረን ነገር ብቻ ነው?

 አይደለም፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብቻ የተነገሩ አይደሉም። ሆኖም ከአምላክ የሚመጡት አብዛኞቹ መልእክቶች በተዘዋዋሪም ቢሆን ስለ ወደፊቱ ጊዜ ይናገራሉ። ለምሳሌ ያህል፣ የአምላክ ነቢያት እስራኤላውያን መጥፎ መንገዳቸውን እንዲተዉ በተደጋጋሚ አስጠንቅቀው ነበር። እነዚህ ማስጠንቀቂያዎች፣ እስራኤላውያን ማስጠንቀቂያውን ከሰሙ ወደፊት የሚያገኙትን በረከት ካልሰሙ ደግሞ ወደፊት የሚጠብቃቸውን ቅጣት የሚገልጹ ነበሩ። (ኤርምያስ 25:4-6) ውጤቱ እስራኤላውያን ለመከተል በሚመርጡት ጎዳና ላይ የተመካ ነበር።—ዘዳግም 30:19, 20

ስለ ወደፊቱ ጊዜ የማይናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች

a በዚህ ወቅት አምላክ ሙሴን በቀጥታ ያነጋገረው ሊመስል ቢችልም አምላክ የሕጉን ቃል ኪዳን ለማስተላለፍ በመላእክት እንደተጠቀመ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።—የሐዋርያት ሥራ 7:53፤ ገላትያ 3:19