ለዮሐንስ የተገለጠለት ራእይ 4:1-11

  • ይሖዋ በሰማይ ላይ ሆኖ በራእይ ታየ (1-11)

    • ይሖዋ በዙፋኑ ላይ ተቀምጦ ነበር (2)

    • በዙፋኖች ላይ የተቀመጡ 24 ሽማግሌዎች (4)

    • አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት (6)

4  ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም፣ በሰማይ የተከፈተ በር ነበር፤ በመጀመሪያ ሲያናግረኝ የሰማሁት ድምፅ እንደ መለከት ድምፅ ያለ ነበር፤ እንዲህም አለኝ፦ “ና ወደዚህ ውጣ፤ መፈጸም ያለባቸውን ነገሮች አሳይሃለሁ።”  ከዚያም ወዲያውኑ የአምላክ መንፈስ ወረደብኝ፦ እነሆም፣ በሰማይ አንድ ዙፋን ተቀምጦ ነበር፤ በዙፋኑም ላይ የተቀመጠ ነበር።+  በዙፋኑም ላይ የተቀመጠው የኢያስጲድ ድንጋይና+ የሰርድዮን ድንጋይ ዓይነት መልክ ነበረው፤ በዙፋኑም ዙሪያ መረግድ የሚመስል ቀስተ ደመና ነበር።+  በዙፋኑ ዙሪያ 24 ዙፋኖች ነበሩ፤ በእነዚህም ዙፋኖች ላይ ነጭ ልብስ የለበሱና በራሳቸው ላይ የወርቅ አክሊል የደፉ 24 ሽማግሌዎች+ ተቀምጠው አየሁ።  ከዙፋኑ መብረቅ፣+ ድምፅና ነጎድጓድ ይወጣ ነበር፤+ በዙፋኑም ፊት የሚነድዱ ሰባት የእሳት መብራቶች ነበሩ፤ እነዚህም ሰባቱን የአምላክ መናፍስት ያመለክታሉ።+  በዙፋኑ ፊት የክሪስታል መልክ ያለው እንደ ብርጭቆ ያለ ባሕር+ የሚመስል ነገር ነበር። በዙፋኑ መካከል* እና በዙፋኑ ዙሪያ ከፊትም ሆነ ከኋላ በዓይኖች የተሞሉ አራት ሕያዋን ፍጥረታት ነበሩ።+  የመጀመሪያው ሕያው ፍጡር አንበሳ ይመስላል፤+ ሁለተኛው ሕያው ፍጡር ወይፈን ይመስላል፤+ ሦስተኛው ሕያው ፍጡር+ የሰው ፊት የሚመስል ፊት ነበረው፤ አራተኛው ሕያው ፍጡር+ ደግሞ የሚበር ንስር ይመስላል።+  እነዚህ አራቱ ሕያዋን ፍጥረታት እያንዳንዳቸው ስድስት ስድስት ክንፎች አሏቸው፤ ክንፎቹ በዙሪያቸውና በውስጥ በኩል በዓይኖች የተሞሉ ናቸው።+ ያለማቋረጥም ቀንና ሌሊት “የነበረው፣ ያለውና የሚመጣው፣+ ሁሉን ቻይ የሆነው ይሖዋ* አምላክ ቅዱስ፣ ቅዱስ፣ ቅዱስ ነው”+ ይላሉ።  ሕያዋን ፍጥረታቱ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠውንና ለዘላለም የሚኖረውን+ ከፍ ከፍ ባደረጉ ቁጥር እንዲሁም እሱን ባከበሩና ባመሰገኑ ቁጥር 10  ሃያ አራቱ ሽማግሌዎች+ በዙፋኑ ላይ በተቀመጠው ፊት ተደፍተው ለዘላለም ለሚኖረው አምልኮ ያቀርባሉ፤ እንዲሁም አክሊላቸውን በዙፋኑ ፊት ጥለው እንዲህ ይላሉ፦ 11  “ይሖዋ* አምላካችን፣ ሁሉንም ነገሮች ስለፈጠርክ+ እንዲሁም ወደ ሕልውና የመጡትም ሆነ የተፈጠሩት በአንተ ፈቃድ ስለሆነ ግርማ፣+ ክብርና+ ኃይል+ ልትቀበል ይገባሃል።”

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በመካከል ከዙፋኑ ጋር።”
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።
ከተጨማሪው መረጃ ላይ ሀ5ን ተመልከት።