በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአምላክን መንግሥት በተመለከተ እውነቱ ምንድን ነው?

የአምላክን መንግሥት በተመለከተ እውነቱ ምንድን ነው?

ኢየሱስ ተከታዮቹን እንደሚከተለው ብለው እንዲጸልዩ አስተምሯቸዋል፦ “በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ። መንግሥትህ ይምጣ። ፈቃድህ በሰማይ እየተፈጸመ እንዳለ ሁሉ በምድርም ላይ ይፈጸም።” (ማቴዎስ 6:9, 10) ለመሆኑ የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው? ምን ነገሮችን ያከናውናል? ይህ መንግሥት እንዲመጣ መጸለይ ያለብንስ ለምንድን ነው?

የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ኢየሱስ ነው።

ሉቃስ 1:31-33 “ስሙንም ኢየሱስ ትዪዋለሽ። እሱም ታላቅ ይሆናል፤ የልዑሉም አምላክ ልጅ ይባላል፤ ይሖዋ አምላክም የአባቱን የዳዊትን ዙፋን ይሰጠዋል፤ በያዕቆብ ቤትም ላይ ለዘላለም ንጉሥ ሆኖ ይገዛል፤ ለመንግሥቱም መጨረሻ የለውም።”

ኢየሱስ በዋነኝነት የሰበከው ስለ አምላክ መንግሥት ነው።

ማቴዎስ 9:35 “ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ፣ የመንግሥቱን ምሥራች እየሰበከ እንዲሁም ማንኛውንም ዓይነት በሽታና ማንኛውንም ዓይነት ሕመም እየፈወሰ በየከተማውና በየመንደሩ ይዞር ጀመር።”

ኢየሱስ የአምላክ መንግሥት የሚመጣው መቼ እንደሆነ የሚጠቁም ምልክት ለደቀ መዛሙርቱ ነግሯቸዋል።

ማቴዎስ 24:7 “ሕዝብ በሕዝብ ላይ፣ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሳልና፤ በተለያየ ስፍራ የምግብ እጥረትና የምድር ነውጥ ይከሰታል።”

በአሁኑ ጊዜ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በዓለም ዙሪያ ስለ አምላክ መንግሥት እየሰበኩ ነው።

ማቴዎስ 24:14 “ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።”