በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቢራቢሮ የሚጓዝበትን አቅጣጫ የሚያውቅበት ዘዴ

ቢራቢሮ የሚጓዝበትን አቅጣጫ የሚያውቅበት ዘዴ

ንድፍ አውጪ አለው?

ቢራቢሮ የሚጓዝበትን አቅጣጫ የሚያውቅበት ዘዴ

ሞናርክ በተርፍላይ የሚባለው ቢራቢሮ ከጤፍ በሚያንሰው አንጎሉ እየተጠቀመ ከካናዳ ተነስቶ በሜክሲኮ እስከሚገኘው አነስተኛ ደን ድረስ 3,000 ኪሎ ሜትር ይጓዛል። ይህ ቢራቢሮ የሚጓዝበትን አቅጣጫ የሚያውቀው እንዴት ነው?

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ ይህ ቢራቢሮ ፀሐይ ያለችበትን ቦታ መሠረት በማድረግ የሚሠራ አቅጣጫ ጠቋሚ ኮምፓስ አለው። ይህ ብቻም አይደለም። እነዚህ ነፍሳት ከፀሐይ እንቅስቃሴ አንጻር አቅጣጫቸውን እንዲያስተካክሉ የሚረዳቸው በቀን ውስጥ 24 ሰዓት የሚሠራ ዝንፍ የማይል “የተፈጥሮ ሰዓት” አላቸው። ኒውሮባዮሎጂስት የሆኑት ዶክተር ስቲቨን ሬፐርት፣ ሞናርክ በተርፍላይ የተባሉት ቢራቢሮዎች “እስካሁን ድረስ ጥናት ከተካሄደባቸው ነፍሳትና እንስሳት ፍጹም የተለየ የጊዜ መቁጠሪያ አላቸው” ብለዋል።

የሳይንስ ሊቃውንት ሞናርክ በተርፍላይ ጊዜን የሚቆጥርበትን መንገድ የበለጠ ማወቃቸው ሰዎችና እንስሳት ስላላቸው “የተፈጥሮ ሰዓት” ተጨማሪ እውቀት እንዲያገኙ ያስችላቸዋል። በተጨማሪም ለነርቭ በሽታዎች አዳዲስ ሕክምናዎችን ለማግኘት ሊረዳቸው ይችላል። ሬፐርት “አንጎል ጊዜንና ቦታን የሚመለከቱ መረጃዎችን ተቀብሎ ስለሚጠቀምበት መንገድ መረዳት እፈልጋለሁ፤ ሞናርክ በተርፍላይ ደግሞ ለዚህ ዓይነተኛ ምሳሌ ነው” ብለዋል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ሞናርክ በተርፍላይ የሚጓዝበትን አቅጣጫ ለማወቅ የሚጠቀምበት ውስብስብ ዘዴ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ከፍተኛ ችሎታ ያለው አንድ ንድፍ አውጪ መኖሩን የሚያሳይ ማስረጃ ነው?

[በገጽ 10 ላይ የሚገኝ ሥዕላዊ መግለጫ/ካርታ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

ሞናርክ በተርፍላይ የተባለው ቢራቢሮ ከካናዳ ተነስቶ በሜክሲኮ እስከሚገኘው አነስተኛ ደን ድረስ 3,000 ኪሎ ሜትር ይጓዛል

[ካርታ]

ካናዳ

ዩናይትድ ስቴትስ

ሜክሲኮ

ሜክሲኮ ሲቲ

[በገጽ 10 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

የዳራ ምስል፦ © Fritz Poelking/age fotostock