በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ንድፍ አውጪ አለው?

የተፈጥሮ ሥርዓቶች

በእንስሳት ላይ የሚታየው አስደናቂ ሥነ ጥበብ—ንድፍ አውጪ አለው?

በእንስሳት ዓለም ላይ አስደናቂ የሆነ ውበትና ሥነ ጥበብ እናያለን።

ፎቶሲንተሲስ—ንድፍ አውጪ አለው?

ፎቶሲንተሲስ ምንድን ነው? ለእኛስ ምን ጥቅም አለው?

የፍጥረታት የኃይል አጠቃቀም—ንድፍ አውጪ አለው?

ፍጥረታት ያላቸው ኃይልን በአግባቡ የመጠቀም ችሎታ ስለ ሕይወት አመጣጥ ምን ይነግረናል?

ብርሃን የሚያበሩ ፍጥረታት—ንድፍ አውጪ አለው?

አንዳንድ እንስሳት ብርሃን የማመንጨት ችሎታ አላቸው፤ እንዲያውም ብርሃን የሚያመነጩት ከሰው ሠራሽ የብርሃን ምንጮች ይበልጥ ኃይል ቆጣቢ በሆነ መንገድ ነው። እንዴት?

የሰው አካል

ኦክስጅን የሚጓጓዝበት መንገድ—ንድፍ አውጪ አለው?

ኦክስጅን በሰውነታችን ውስጥ ስለሚጓጓዝበትና ጥቅም ላይ ስለሚውልበት አስደናቂ ሥርዓት ተመልከት።

የሰው አካል ያለው ቁስልን የመጠገን ችሎታ

የሳይንስ ሊቃውንት ይህን ችሎታ በመኮረጅ አዲስ ዓይነት የፕላስቲክ ዕቃዎች የሠሩት እንዴት ነው?

በምድር ላይ የሚኖሩ እንስሳት

የዝሆን ኩምቢ—ንድፍ አውጪ አለው?

የዝሆን ኩምቢ ያለው ድንቅ ቅልጥፍና ተመራማሪዎችን ያስገረመ ነው። ውስብስብና ረቂቅ ለሆነው አፈጣጠሩ ሚስጥሩ ምን እንደሆነ ተመልከት።

የአርክቲኩ የመሬት አደሴ ቁኒ አንጎል—ንድፍ አውጪ አለው?

ይህ እንስሳ ለወራት በእንቅልፍ ከቆየ በኋላ አንጎሉ መልሶ የሚያንሰራራው እንዴት ነው?

የባሕር አቆስጣ ፀጉር—ንድፍ አውጪ አለው?

በቀዝቃዛ ውኃ ውስጥ የሚኖሩ አንዳንድ አጥቢ እንስሳት ከቆዳቸው ሥር ብርድ ለመከላከል የሚረዳ ወፍራም ስብ አላቸው። የባሕር አቆስጣ ግን ለየት ያለ የብርድ መከላከያ አለው።

የድመት ምላስ—ንድፍ አውጪ አለው?

የቤት ድመቶች ነቅተው ካሉበት ጊዜ ውስጥ 24 በመቶውን ራሳቸውን በማስዋብ ሊያሳልፉ ይችላሉ። ይህ የጽዳት ልማዳቸው ውጤታማ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው?

የድመት ጺም ያለው ጥቅም—ንድፍ አውጪ አለው?

የሳይንስ ሊቃውንት፣ የድመት ጺሞችን ንድፍ በመኮረጅ ኢዊስከርስ የተባሉ ጠቋሚ መሣሪያዎች ያሏቸውን ሮቦቶች ለመሥራት ጥረት እያደረጉ ያሉት ለምንድን ነው?

የውሾች የማሽተት ችሎታ

የሳይንስ ሊቃውንት የውሾችን የማሽተት ችሎታ ለመኮረጅ እየሞከሩ ያሉት ለምንድን ነው?

የፈረስ እግር—ንድፍ አውጪ አለው?

የምሕንድስና ባለሙያዎች የፈረስ እግርን ንድፍ መኮረጅ ያቃታቸው ለምንድን ነው?

በጆሮዋ “የምታየው” የሌሊት ወፍ—ንድፍ አውጪ አለው?

የሌሊት ወፍ ዓይኗን ሳትጠቀም “ማየት” የቻለችው እንዴት ነው?

ዛጎል አልባ ቀንድ አውጣ የሚያመነጨው የሚያጣብቅ ዝልግልግ ፈሳሽ

ዛጎል አልባ ቀንድ አውጣ የሚያመነጨውን ማጣበቂያ በመኮረጅ የተሠራው ሙጫ ሁሉም የቀዶ ሕክምና ባለሙያዎች አዘውትረው የሚጠቀሙበት መሣሪያ እንደሚሆን እንዲሁም ወደፊት በቀዶ ሕክምና ወቅት ስፌትና ስቴፕለር መጠቀም ላያስፈልግ እንደሚችል ይታሰባል።

የውኃ ውስጥ ሕይወት

የሻርክ ቆዳ—ንድፍ አውጪ አለው?

በሻርክ ቆዳ ላይ ተሕዋስያን የማይጣበቁት ለምንድን ነው?

ረጅም ርቀት የሚጠልቁ ዓሣ ነባሪዎች—ንድፍ አውጪ አለው?

አየር የሚተነፍሱ አጥቢ እንስሳት የሆኑት እነዚህ ዓሣ ነባሪዎች ረጅም ርቀት መጥለቅና ለረጅም ሰዓት ሳይተነፍሱ መቆየት የቻሉት እንዴት ነው?

የሃምፕባክ ዓሣ ነባሪ መቅዘፊያ

የዚህ ግዙፍ እንስሳ መቅዘፊያ የሚሠራበት መንገድ ዛሬ የምታያቸውን አንዳንድ መሣሪያዎች ንድፍ ለማውጣት አስተዋጽኦ ያበረከተው እንዴት እንደሆነ አንብብ።

ፓይለት ዌል የተባለው ዓሣ ነባሪ ቆዳውን የሚያጸዳበት መንገድ

ይህ ዓሣ ነባሪ ያለው ለየት ያለ ችሎታ የመርከብ ኩባንያዎችን ትኩረት የሳበው ለምንድን ነው?

ዶልፊኖች አካባቢያቸውን ለማወቅ የሚጠቀሙበት ዘዴ—ንድፍ አውጪ አለው?

ሳይንቲስቶች እነዚህ እንስሳት ያላቸውን አስገራሚ የሆነ አካባቢን የመቃኘትና የማወቅ ችሎታ በመኮረጅ ተመሳሳይ ነገር ማድረግ የሚችሉ መሣሪያዎችን ለመሥራት እየሞከሩ ነው።

የሃግፊሽ ልፋጭ—ንድፍ አውጪ አለው?

ለአዳኝ ዓሦች መከራ ቢሆንም የሳይንቲስቶችን ቀልብ ገዝቷል። ለምን?

የባሕር ኪያር አስገራሚ ቆዳ

የባሕር ኪያር እንደ ሁኔታው የሚለዋወጥ ቆዳ ሊኖረው የቻለው እንዴት ነው?

ግራኒየን የተባሉት ዓሣዎች እንቁላል የሚጥሉበት ዘዴ—ንድፍ አውጪ አለው?

እንቁላላቸውን የሚጥሉበት ጊዜና መንገድ ለእንቁላሎቹ ደህንነት የሚጠቅመው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

የሊምፔት ጥርስ

የሊምፔት ጥርስ ከሸረሪት ድር ይበልጥ ሊጠነክር የቻለው እንዴት ነው?

የባርናክሎች ሙጫ

የባርናክሎች ሙጫ ከየትኛውም ሰው ሠራሽ ሙጫ የበለጠ ኃይል አለው። ባርናክሎች እርጥበት ካላቸው ነገሮች ጋር የሚጣበቁበት መንገድ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ እንቆቅልሽ ሆኖ ቆይቷል።

የባሕር መስል ራሱን የሚያጣብቅበት መንገድ

የባሕር መስሎች በክሮች አማካኝነት ራሳቸውን ያጣብቃሉ። የእነዚህን ክሮች ንድፍ መረዳት በሕንፃዎች ላይ መሣሪያዎችን ለመግጠምና ጅማትን ከአጥንት ጋር ለማያያዝ ያስችላል።

የዛጎል ቅርጽ

ዛጎሎች ያላቸው ቅርጽና አሠራራቸው በውስጣቸው የሚኖሩትን ሞለስኮች ከአደጋ ይጠብቃቸዋል።

ከትልፊሽ—የባሕር ውስጥ እስስት

መሐንዲሶች ከትልፊሽ ያለውን ችሎታ በመኮረጅ ቀለማቸውን በቅጽበት የሚቀይሩ ልብሶች ለመሥራት እየሞከሩ ነው።

ብርሃን አመንጪው የሃዋይ ቦብቴይል ስኩዊድ—ንድፍ አውጪ አለው?

እንስሳው የራሱን ብርሃን የሚፈጥረው ለማየት ወይ ለመታየት አይደለም።

አስደናቂው የኦክቶፐስ እጅ​—ንድፍ አውጪ አለው?

መሐንዲሶች የኦክቶፐስን እጆች በመመልከት፣ አስገራሚ ችሎታዎች ያሉት የሮቦት እጅ ሠርተዋል።

“የማየት ችሎታ” ያላቸው የብሪትል ስታር አጥንቶች

በውቅያኖስ ሥር በሚገኙ ቋጥኞች ላይ ስለሚኖር የባሕር ፍጥረት፣ አስደናቂ እውነታዎችን እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

የባሕር ፈረስ ጅራት—ንድፍ አውጪ አለው?

የባሕር ፈረስ የተባለውን ዓሣ ለየት ያለ ጅራት በመኮረጅ ወደፊት የተሻሉ ሮቦቶችን መሥራት የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ተመልከት።

እጅብ ብለው የሚዋኙ ዓሦች

የመኪና አደጋዎችን መቀነስ ስለሚቻልበት መንገድ ከዓሦች ምን ልንማር እንችላለን?

የሬሞራ መጣበቂያ—ንድፍ አውጪ አለው?

ይህ ዓሣ በሌሎች የባሕር ፍጥረታት ላይ ሙጭጭ ብሎ እንዲጣበቅ የረዳው ምንድን ነው?

ማንታ ሬይ የተባለው ዓሣ የማጣሪያ ሥርዓት​—ንድፍ አውጪ አለው?

ማንታ ሬይ የተባለው ዓሣ ከማጣሪያ ቀዳዳዎቹ በጣም ያነሱ የባሕር ተክሎችን ከውኃው ለይቶ ማስቀረት የሚችለው እንዴት ነው?

ወፎች

የሃሚንግበርድ ምላስ—ንድፍ አውጪ አለው?

ይህች ትንሽ ወፍ የአበባ ማር ለመቅሰም የምትጠቀምበት ዘዴ ቀልጣፋና ኃይል ቆጣቢ ነው።

ጋኔቶች ወደ ውኃ የሚጠልቁበት መንገድ—ንድፍ አውጪ አለው?

እነዚህ ትላልቅ የባሕር ወፎች ከመሬት ስበት 20 እጥፍ የሚበልጥ ኃይል ቢያርፍባቸውም ጉዳት የማይደርስባቸው ለምንድን ነው?

ቀለማቸው የማይደበዝዝ ወፎች

መቼም ስለማይደበዝዘው የወፎች ቀለም የተደረገው ጥናት የተሻሉ ቀለሞችንና ጨርቆችን መሥራት እንዲቻል መንገድ እየጠረገ ያለው እንዴት ነው?

የጉጉት ክንፍ—ንድፍ አውጪ አለው?

በጉጉቶች ክንፍ ላይ የሚታየው የረቀቀ ንድፍ በነፋስ የሚንቀሳቀሱ ሞተሮች የሚያወጡትን ድምፅ ለመቀነስ የሚረዳ ቁልፍ ይዟል።

ወደ ላይ የሚቀለበስ ክንፍ ያላቸው ወፎች

የአውሮፕላን መሐንዲሶች የእነዚህን ወፎች ክንፍ ንድፍ በመኮረጅ የሠሩት ነገር በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ 7,600 ሚሊዮን ሊትር የሚሆን ነዳጅ እንዳይባክን አስተዋጽኦ አድርጓል።

የኤምፐረር ፔንግዊን ባለ ላባ ልብስ—ንድፍ አውጪ አለው?

የባሕር ውስጥ የሥነ ሕይወት ተመራማሪዎች፣ የዚህን ወፍ ላባዎች በተመለከተ የደረሱበት ነገር ምንድን ነው?

የዋንደሪንግ አልባትሮስ ኃይል ቆጣቢ የበረራ ዘዴ

ይህ ወፍ ክንፉን አንድ ጊዜም ሳያራግብ ለበርካታ ሰዓታት መብረር የሚችለው እንዴት እንደሆነ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

የባር ቴይልድ ጎድዊት አቅጣጫ የማወቅ ችሎታ

ይህ ወፍ ከቦታ ወደ ቦታ በሚፈልስበት ወቅት ለስምንት ቀናት ስለሚያደርገው አስደናቂ ጉዞ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ማሊ የተባሉት ወፎች ጎጆ—ንድፍ አውጪ አለው?

እነዚህ ወፎች የአትክልት ቁልል በመሥራት ለእንቁላሎቻቸው ምቹ መፈልፈያ ቦታ ያዘጋጃሉ። ወቅቶች ቢፈራረቁም እነዚህ ወፎች ጎጇቸው ውስጥ ዓመቱን ሙሉ ተመሳሳይ የሙቀት መጠን እንዲኖር የሚያደርጉት እንዴት ነው?

በምድር ላይ የሚሳቡ፣ በውኃ ውስጥም ሆነ በየብስ ላይ የሚኖሩ እንስሳት

ቶርኒ ዴቭል የተባለው እንሽላሊት ውኃ የሚስብ ቆዳ

ይህ እንሽላሊት ውኃ በእግሮቹ በኩል ሽቅብ ወደ አፉ እንዲሄድ የሚያደርገው እንዴት ነው?

የአጋማ ጅራት—ንድፍ አውጪ አለው?

ይህ የእንሽላሊት ዝርያ ከወለል ላይ ተስፈንጥሮ ቀጥ ያለ ግድግዳ ላይ በቀላሉ ማረፍ የሚችለው እንዴት ነው?

የአዞ መንጋጋ—ንድፍ አውጪ አለው?

የአዞ የመንከስ ኃይሉ ከአንበሳ ወይም ከነብር ጋር ሲወዳደር ሦስት እጥፍ ይበልጣል። ያም ሆኖ መንጋጋው አንድ ነገር ሲነካው የመለየት ኃይሉ ከጣታችን ጫፍ እንኳ ይበልጣል። ይህ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው?

የእባብ ቆዳ

እባቦች ሸካራ ቅርፊት ባለው የዛፍ ግንድ ላይ መውጣት እንዲሁም ሸካራ የሆነ አሸዋ ቆፍረው መግባት ይችላሉ። ለመሆኑ ቆዳቸው ይህን ያህል ጠንካራ ሊሆን የቻለው እንዴት ነው?

እንቁላሎቿን ሆዷ ውስጥ የምትታቀፈው እንቁራሪት የመራቢያ ሥርዓት

የዝግመተ ለውጥ አራማጅ የሆኑ ሰው በእንቁራሪቷ የመራቢያ ሥርዓት ላይ አዝጋሚና በጊዜ ሂደት የተካሄደ ለውጥ ተከስቷል ብሎ ማሰብ ጨርሶ የማይመስል ነገር እንደሆነ የገለጹት ለምንድን ነው?

የጃፓን የዛፍ እንቁራሪቶች ጥሪ—ንድፍ አውጪ አለው?

ወንድ የጃፓን የዛፍ እንቁራሪቶች ሴት እንቁራሪቶችን ለመማረክ ከሚያሰሙት ጥሪ በስተ ጀርባ ያለው ሚስጥር ምንድን ነው?

ነፍሳት

የንቦች የበረራ ጥበብ—ንድፍ አውጪ አለው?

አንዲት ትንሽ ፍጥረት ተሞክሮ ካላቸው የአውሮፕላን አብራሪዎች የተሻለ የበረራ ጥበብ ሊኖራት የቻለው እንዴት ነው?

ንብ የምትፈልገው ቦታ ላይ ለማረፍ የምትጠቀምበት ዘዴ

ንቦች የሚፈልጉበት ቦታ ላይ ለማረፍ የሚጠቀሙበት ዘዴ በራሪ ሮቦቶችን የሚቆጣጠሩ ፕሮግራሞችን ለመሥራት አመቺ የሆነው ለምንድን ነው?

የማር እንጀራ—ንድፍ አውጪ አለው?

የሒሳብ ሊቃውንት፣ ንቦች ቦታን በተሻለ መንገድ ለመጠቀም የሚያስችላቸውን ንድፍ ሙሉ በሙሉ የተረዱት በ1999 ነው፤ ለመሆኑ ይህ ብልሃት ምንድን ነው?

ጉንዳኖች የትራፊክ መጨናነቅን የሚከላከሉበት መንገድ

ጉንዳኖች የትራፊክ መጨናነቅን የሚከላከሉት እንዴት ነው?

የጉንዳን አንገት

ጉንዳኖች ከራሳቸው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ክብደት መሸከም የሚችሉት እንዴት ነው?

ካርፔንተር አንት የተባለው ጉንዳን አንቴናውን የሚያጸዳበት መንገድ

ይህ ትንሽ ነፍሳት በሕይወት መኖሩን እንዲቀጥል የግድ ንጽሕናውን መጠበቅ ያስፈልገዋል። ታዲያ ይህን ወሳኝ ተግባር የሚያከናውነው እንዴት ነው?

የሰሃራው ብርማ ጉንዳን ሙቀት የሚከላከልበት መንገድ

የሰሃራው ብርማ ጉንዳን ሙቀትን የመቋቋም ከፍተኛ ችሎታ ካላቸው በየብስ የሚኖሩ ፍጥረታት መካከል አንዱ ነው። ይህ ጉንዳን ከፍተኛ ሙቀትን መቋቋም የሚችለው እንዴት ነው?

የፒሪዮዲካል ሲካዳ የሕይወት ዑደት

አስገራሚ የሕይወት ዑደት ያላቸው እነዚህ ነፍሳት ብቅ የሚሉት በ13 ወይም በ17 ዓመት አንድ ጊዜ ለጥቂት ሳምንታት ነው።

የኢሰስ ሊፍሆፐር እግር ላይ ያሉ ጥርሶች

ፌንጣው አቅጣጫውን ሳይስት በኃይል እንዲዘል የሚያስችሉት ወሳኝ ነገሮች ናቸው።

አንበጦች እንቅስቃሴያቸውን የሚቆጣጠሩበት የነርቭ ሴል

እየበረሩ ያሉ አንበጦች ግጭት እንዳይፈጠር የሚከላከሉት እንዴት ነው?

አስደናቂ የሆነው የእንጭርሪት የመስማት ችሎታ

የዚህች ትንሽ ነፍሳት ጆሮ የሚሠራው፣ የሰው ልጆች ጆሮ ከሚሠራበት መንገድ ጋር በሚመሳሰል መልኩ ነው። ስለዚህች ነፍሳት ልዩ የሆነ የመስማት ችሎታ የሚደረገው ምርምር ለዘመናዊው ሳይንስ እና ምሕንድስና አስተዋጽኦ የሚያበረክተው እንዴት ነው?

የሞናርክ ቢራቢሮ ፍልሰት—ንድፍ አውጪ አለው?

አስደናቂና ውስብስብ የሆነው የሞናርክ ቢራቢሮ ፍልሰት ንድፍ አውጪ እንዳለ ይመሠክራል?

የቢራቢሮ ክንፍ

ብሉ ሞርፎ የተባለው ቢራቢሮ ክንፍ እንዲሁ ሲታዩ ልሙጥ ይምሰሉ እንጂ በአጉሊ መነጽር ብቻ የሚታዩ የተነባበሩ ቅርፊቶች አሉት። ዓላማቸው ምንድን ነው?

ብርሃን የመሰብሰብ ችሎታ ያለው የቢራቢሮ ክንፍ

አንዳንድ የቢራቢሮ ዝርያዎች ይህ ችሎታ እንዲኖራቸው ያደረገው ክንፋቸው ጥቁር መሆኑ ብቻ አይደለም።

ካቤጅ ኋይት ቢራቢሮ ክንፏን የምትዘረጋበት መንገድ

ካቤጅ ኋይት ቢራቢሮ ያላት ችሎታ ተመራማሪዎች ይበልጥ ውጤታማ የሆኑ የፀሐይ ኃይል መቀበያ መሣሪያዎችን እንዲሠሩ ያስቻላቸው እንዴት ነው?

የሙጫ እሳት ራት አስደናቂ የመስማት ችሎታ

የዚህ የእሳት ራት ጆሮ የተሠራበት መንገድ ያልተወሳሰበ ቢሆንም በዓለም ላይ ካሉት ፍጥረታት ሁሉ የተሻለ የመስማት ችሎታ አለው።

የጥንዚዛ ቅርፊት​—ንድፍ አውጪ አለው?

ይህ ጥንዚዛ ይህን ያህል ከባድ ጭነት የመቋቋም ችሎታ ሊኖረው የቻለው እንዴት ነው?

ጥቁር የእሳት ጥንዚዛ ያሉት ጠቋሚዎች

መሐንዲሶችና ተመራማሪዎች፣ ልዩ ችሎታ ካለው ከዚህ ጥንዚዛ ምን መማር ይችላሉ?

እበት ለቃሚው ጥንዚዛ ያለው አቅጣጫ የማወቅ ችሎታ

እበት ለቃሚ ጥንዚዛ አቅጣጫ የሚያውቀው እንዴት ነው? ሰዎች ከዚህ ጥንዚዛ ምን ሊማሩ ይችላሉ?

የፎቱርየስ አብሪ ጥንዚዛ መብራት—ንድፍ አውጪ አለው?

የሳይንስ ሊቃውንት፣ ከዚህች ትንሽ ነፍሳት አፈጣጠር የወሰዱት መረጃ በብዙ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያዎች ላይ የሚገኙትን ብርሃን አመንጪ ዳዮዶችን ይበልጥ ውጤታማ እንዲሆን ለማድረግ የረዳቸው እንዴት ነው?

የዝንቦች ሃልቲር

ዝንቦችን መያዝ በጣም አስቸጋሪ የሆነው ለምን እንደሆነ አስበህ ታውቃለህ? የሳይንስ ሊቃውንት የደረሱበትን ግኝት ለማወቅ ይህን ርዕስ እንድታነብ እንጋብዝሃለን።

ፍሩት ፍላይ የተባለችው ዝንብ አስደናቂ የበረራ ችሎታ

እነዚህ ነፍሳት እንደ ጦር ጄት በአየር ላይ የመገለባበጥ ችሎታ አላቸው፤ ሆኖም ይህን የሚያደርጉት ከአንድ ሴኮንድ ባነሰ ጊዜ ውስጥ ነው።

ሸረሪት

የተስፈንጣሪው ሸረሪት ብዥ ያለ እይታ

ይህ ሸረሪት የሚዘልለውን ርቀት በትክክል የሚያሰላው እንዴት ነው?ተመራማሪዎች ይህ ሸረሪት የሚጠቀምበትን ዘዴ ለመቅዳት የሚሞክሩትስ ለምንድን ነው?

የሸረሪት የማጣበቅ ችሎታ ሚስጥር

የሸረሪት ድር እንደ አስፈላጊነቱ በኃይል የሚያጣብቅ ወይም በቀላሉ የሚላቀቅ ሙጫ አለው። ይህ ሊሆን የቻለው እንዴትና ለምን እንደሆነ ተመልከት።

ዕፀዋት

የፖሜሎ ልጣጭ ያለው ግጭት የመቋቋም ችሎታ—ንድፍ አውጪ አለው?

ሳይንቲስቶች የፖሜሎ ፍሬ ያለውን ግጭት የመቋቋም ችሎታ ለመኮረጅ እየሞከሩ ያሉት እንዴት ነው?

የፖሊያ ቤሪ ደማቅ ሰማያዊ ቀለም

ፖሊያ ቤሪ በውስጡ ሰማያዊ ቀለም እንዲኖረው የሚያደርግ ንጥረ ነገር ባይኖረውም በየትኛውም ተክል ላይ የማይታይ ደማቅ ሰማያዊ ቀለም አለው። ታዲያ ይህን የመሰለ አስደናቂ ቀለም ሊኖረው የቻለው እንዴት ነው?

የዳንዴሊየን ዘር የበረራ ጥበብ—ንድፍ አውጪ አለው?

የዳንዴሊየን ዘር የበረራ ጥበብ በኃይል አጠቃቀም ረገድ፣ ዘመኑ ካፈራቸው ፓራሹቶች በአራት እጥፍ የተሻለ ነው፤ የተሻለ ተደላድሎ የመንሳፈፍ ችሎታም አለው።

የዕፀዋት የሒሳብ ችሎታ

ተመራማሪዎች የሰናፍጭ ተክል አስገራሚ ችሎታ እንዳለው ደረሱበት።

ረቂቅ ፍጥረታት

ዲ ኤን ኤ ያለው መረጃ የመያዝ አቅም

ዲ ኤን ኤ “ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ሃርድ ድራይቭ” የሚል ስያሜ ተሰጥቶታል። እንዲህ ተብሎ የተጠራው ለምን እንደሆነ አንብብ።

ዘይት የሚያሟሙ ረቂቅ ተሕዋስያን

ከዘመናዊ ቴክኖሎጂ ጋር ሲነጻጸሩ የፈሰሰ ዘይት በማጽዳት ረገድ ምን ያህል ውጤታማ ናቸው?