በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የጉጉት ላባ

የጉጉት ላባ

ንድፍ አውጪ አለው?

የጉጉት ላባ

የበረራ መሐንዲሶች ከሌሊት ጉጉት የሚያስቀናቸው አንድ ነገር አለ። ይኸውም ምንም ድምፅ ሳያሰማ የሚበር መሆኑ ነው። “ከዚህ ወፍ ሌላ ድምፅ ሳያሰማ መብረር የሚችል ሌላ ወፍ የለም” በማለት የናሽናል ጂኦግራፊክ ድረ ገጽ ይናገራል። ጉጉት ምንም ድምፅ ሳያሰማ እንዲበር ያስቻለው ሚስጥር ምንድን ነው?

እስቲ የሚከተለውን አስብ፦ አብዛኞቹ ወፎች በሚበሩበት ጊዜ ከክንፋቸው ጋር እየተጋጨ የሚያልፈው አየር ከፍተኛ ድምፅ ይፈጥራል። ከጉጉት ጋር በተያያዘ ግን ሁኔታው የተለየ ነው። የተሞነጫጨሩት የጉጉት ላባዎች ወፉ ክንፎቹን ወደታች በሚመታበት ጊዜ በአየሩ ግፊት ምክንያት የሚፈጠረውን ድምፅ ውጦ ማስቀረት የሚችል ጠርዝ አላቸው። በጉጉቱ አካል ላይ የሚገኙት ስስ ላባዎች ደግሞ የቀረውን ድምፅ ውጠው ያስቀራሉ።

የአውሮፕላን ንድፍ አውጪዎች፣ ጉጉት ድምፅ ሳያሰማ እንዲበር የሚያስችለውን ሚስጥር ይበልጥ ቢያውቁ ደስ ይላቸው ነበር። አነስተኛ የድምፅ መጠን ያላቸው አውሮፕላኖች ቢኖሩ ኖሮ ጥብቅ የሆነ የድምፅ መጠን ቁጥጥር የሚያደርጉ የአውሮፕላን ማረፊያዎች በሌሊትም ሆነ በማለዳው ሰዓት አውሮፕላኖች እንዲበሩም ሆነ እንዲያርፉ ይፈቅዱ ነበር። አሁንም ቢሆን በዚህ ረገድ አንዳንድ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ዕቅድ ተይዟል። በእንግሊዙ የሳውዝሃምፕተን ዩኒቨርሲቲ የበረራ ምሕንድስና ፕሮፌሰር የነበሩት ጄፍሪ ሊሌይ “አሁን እንዲህ ያሉ ማሻሻያዎችን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደምንችል እያወቅን ነው” በማለት ተናግረዋል። አክለውም እንዲህ ዓይነቱን ድምፅ አልባ አውሮፕላን ለመሥራት አሥርተ ዓመታት ሊፈጅ እንደሚችል ተናግረዋል።

ታዲያ ምን ይመስልሃል? ድምፅ ውጦ ማስቀረት የሚችለው የጉጉት ላባ በአጋጣሚ የተገኘ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[በገጽ 23 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በስተግራ የሚገኘውን የጉጉት ላባ በስተቀኝ ካለው የጭልፊት ላባ ጋር አወዳድር

[በገጽ 23 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

Long-eared owl: © Joe McDonald/Visuals Unlimited; barn owl sequence: © Andy Harmer/Photo Researchers, Inc.; feather comparison: Courtesy of Eike Wulfmeyer/Wikimedia/GFDL