በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ቤተሰብ የሚወያይበት

ከዚህ ሥዕል ውስጥ የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው?

ዘፍጥረት 1:21-28ን አንብብ። ከዚያም ሥዕሉን ተመልከት። በጥቅሱ ውስጥ ከተገለጹት መካከል የጎደሉት ነገሮች ምንድን ናቸው? መልስህን ከታች ባሉት ክፍት ቦታዎች ላይ ጻፍ። እንዲሁም ሥዕሉ የተሟላ እንዲሆን ነጥቦቹን በመስመር ካገናኘህ በኋላ ተስማሚ የሆነውን ቀለም ቀባ።

1. ․․․․․

2. ․․․․․

[ሰንጠረዥ]

(ጽሑፉን ተመልከት)

ለውይይት፦

አምላክ “ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር” ያለው ማንን ነበር?

ፍንጭ፦ ዮሐንስ 17:1, 5⁠ን እና ቆላስይስ 1:15, 16⁠ን አንብብ።

ሰዎች በአምላክ መልክ ተፈጥረዋል ሊባል የሚችለው እንዴት ነው?

ፍንጭ፦ ቆላስይስ 3:10⁠ን እና 1 ጴጥሮስ 1:16⁠ን አንብብ።

ይሖዋና ኢየሱስ ካላቸው ባሕርያት መካከል አንተን ይበልጥ የሚስቡህ የትኞቹ ናቸው? እነሱ ያላቸውን ባሕርይ ማንጸባረቅ የምትችለውስ እንዴት ነው?

ፍንጭ፦ ኤፌሶን 4:31, 32⁠ን እና 1 ዮሐንስ 4:7, 8⁠ን አንብብ።

ቤተሰብን የሚያሳትፍ፦

በጣም የምትወዳቸውን አምስት እንስሳት ስም ጻፍ። ከዚያም የእንስሳቱን መልክ፣ ድምፅ ወይም ድርጊት መሠረት በማድረግ ልክ እንደ አዳም አዳዲስ ስም አውጣላቸው። ያወጣሃቸውን አዳዲስ ስሞች ለቤተሰቦችህ ካነበብክላቸው በኋላ የትኛው እንስሳ እንደሆነ እንዲገምቱ አድርግ።

ካርድ በመሰብሰብ መማር

ቆርጠህ አውጣውና ለሁለት አጥፈህ አስቀምጠው

የመጽሐፍ ቅዱስ ካርድ 19 ጳውሎስ

ጥያቄ

ሀ. ጳውሎስ አገልግሎቱን ሲያከናውን ራሱን የሚያስተዳድረው ․․․․․ በመስፋት ነበር።

ለ. ሐዋርያው ጳውሎስ ሰዎችን “በአደባባይና . . .” ያስተምር ነበር።

ሐ. ጳውሎስ ․․․․․ የተባለውን ወጣት ከሞት አስነስቷል።

[ሰንጠረዥ]

4026 ዓ.ዓ. አዳም ተፈጠረ

ጳውሎስ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ዓ.ም. ኖሯል

1 ዓ.ም.

98 ዓ.ም. የመጨረሻው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ተጻፈ

[ካርታ]

የተወለደው በጠርሴስ ነው። በአውሮፓና በትንሿ እስያ ሚስዮናዊ ሆኖ አገልግሏል።

አውሮፓ

ሮም

ትንሿ እስያ

ጠርሴስ

ኢየሩሳሌም

ጳውሎስ

አጭር የሕይወት ታሪክ፦

ቀድሞ የክርስቲያኖች አሳዳጅ የነበረና በኋላ ክርስትናን ተቀብሎ የአሕዛብ ሐዋርያ የሆነ ሰው ነው። ይሖዋ 14 የክርስቲያን ግሪክኛ ቅዱሳን መጻሕፍትን እንዲጽፍ አድርጎታል። ጳውሎስ በሚስዮናዊ አገልግሎቱ ወቅት በሺህ የሚቆጠሩ ኪሎ ሜትሮችን ተጉዟል፤ እንዲሁም በአውሮፓና በትንሿ እስያ ጉባኤዎችን አቋቁሟል።—ሮም 11:13፤ 1 ጢሞቴዎስ 1:12-16

መልስ

ሀ. ድንኳን—የሐዋርያት ሥራ 18:3-5

ለ. “. . . ከቤት ወደ ቤት” —የሐዋርያት ሥራ 20:20

ሐ. አውጤኪስ—የሐዋርያት ሥራ 20:7-12

ሕዝቦችና አገሮች

3. ማቴ እና ናኣ እንባላለን፤ የ7 እና የ8 ዓመት ልጆች ስንሆን የምንኖረው በጆርጂያ ሪፑብሊክ ነው። በጆርጂያ ምን ያህል የይሖዋ ምሥክሮች ያሉ ይመስልሃል? 10,000፣ 17,000 ወይስ 26,000?

4. የምንኖርበትን አገር የሚጠቁመው ፊደል የትኛው ነው? በፊደሉ ላይ አክብብ፤ ከዚያም አንተ በምትኖርበት አገር ላይ ምልክት አድርግ፤ የምትኖርበት አገር ከጆርጂያ በጣም ይርቃል?

ለልጆች የቀረበ የሥዕል ጥያቄ

ከዚህ መጽሔት ውስጥ እነዚህን ሥዕሎች ማግኘት ትችላለህ? እያንዳንዱ ሥዕል ምን እንደሚያሳይ በራስህ አባባል ግለጽ።

“ቤተሰብ የሚወያይበት” የሚለውን ዓምድ ተጨማሪ ቅጂ ለማግኘት www.ps8318.com ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማተም ይቻላል።

● “ቤተሰብ የሚወያይበት” መልሶች በገጽ 26 ላይ ይገኛሉ

በገጽ 30 እና 31 ላይ ያሉት ጥያቄዎች መልስ

1. ክንፍ ያለው በራሪ ፍጥረት

2. የዱር አራዊት

3. 17,000

4.