በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“በሕይወት የመኖራችን ዓላማ ምንድን ነው?”

“በሕይወት የመኖራችን ዓላማ ምንድን ነው?”

“በሕይወት የመኖራችን ዓላማ ምንድን ነው?”

የኖቤል ሽልማት አሸናፊ የሆኑትና ከናዚ እልቂት በሕይወት የተረፉት ኤሊ ቪዝል “የሰው ልጅ መልስ ሊያገኝለት የሚገባው እጅግ አንገብጋቢ የሆነ ጥያቄ” በማለት ጠርተውታል። ይህም ጥያቄ “በሕይወት የመኖራችን ዓላማ ምንድን ነው?” የሚል ነው።

አንተስ እንዲህ ብለህ ጠይቀህ ታውቃለህ? ብዙ ሰዎች ይህንን ጥያቄ ቢያነሱም መልስ አላገኙለትም። አርኖልድ ቶይንቢ የተባሉ እንግሊዛዊ ታሪክ ጸሐፊ የሕይወትን ትርጉም ለማወቅ ባደረጉት ጥረት የደረሱበትን መደምደሚያ እንዲህ በማለት ጽፈዋል:- “የሰው ሕይወት እውነተኛ ዓላማ አምላክን ማወደስና ለዘላለም በእርሱ እየተደሰቱ መኖር ነው።”

የሚገርመው ነገር፣ ከሦስት ሺህ ዓመት በፊት የኖረ ስለ ሕይወት በጥልቅ ያስብ የነበረ አንድ ሰው ለዚህ መሠረታዊ ጥያቄ መልስ ሰጥቷል። ጠቢቡ ንጉሥ ሰሎሞን እንዲህ ብሏል:- “እነሆ፤ ሁሉ ነገር ከተሰማ ዘንድ፣ የነገሩ ሁሉ ድምዳሜ ይህ ነው፤ እግዚአብሔርን ፍራ፤ ትእዛዛቱንም ጠብቅ፤ ይህ የሰው ሁለንተናዊ ተግባሩ ነውና።”—መክብብ 12:13

የአምላክ ልጅ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ መሠረታዊ ሥርዓት ተስማምቷል። ኢየሱስ ምድር በነበረበት ጊዜ በሰማይ ያለውን አባቱን ለማስከበር የሚችለውን ሁሉ አድርጓል። ኢየሱስ ፈጣሪውን በማገልገሉ ደስተኛ መሆን ችሏል። ይህን ማድረጉ እስከ መጨረሻ እንዲጸና የረዳው ሲሆን “የእኔ ምግብ የላከኝን ፈቃድ ማድረግና ሥራውን መፈጸም ነው” በማለት ሊናገር ችሏል።—ዮሐንስ 4:34

ታዲያ በሕይወት የመኖራችን ዓላማ ምንድን ነው? ልክ እንደ ኢየሱስ፣ ሰሎሞንና ሌሎች የአምላክ አገልጋዮች ሁሉ እኛም የአምላክን ፈቃድ በማድረግ እውነተኛ ትርጉም ያለው ሕይወት ልንመራና ዘላቂ ደስታ ልናገኝ እንችላለን። አምላክን “በመንፈስና በእውነት” ማምለክ የሚቻለው እንዴት እንደሆነ ለማወቅ ትፈልጋለህ? (ዮሐንስ 4:24) በአካባቢህ የሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች “በሕይወት የመኖራችን ዓላማ ምንድን ነው?” ለሚለው ጥያቄ መልስ እንድታገኝ ሊረዱህ ፈቃደኞች ናቸው።