በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

‘ስምህን አሳውቄአለሁ’

‘ስምህን አሳውቄአለሁ’

‘ስምህን አሳውቄአለሁ’

“ከዓለም ለሰጠኸኝ ሰዎች ስምህን ገልጬላቸዋለሁ። . . . ስምህን ለእነሱ አሳውቄአለሁ፤ ደግሞም አሳውቃለሁ።”​—ዮሐንስ 17:6, 26

ይህ ምን ማለት ነው? ኢየሱስ በአገልግሎቱ ላይ የአምላክን ስም በመጠቀም ይህ ስም እንዲታወቅ አድርጓል። ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ያደርገው እንደነበረው ከቅዱሳን መጻሕፍት ላይ በሚያነብበት ጊዜ የአምላክን የግል ስም ይጠራ ነበር። (ሉቃስ 4:16-21) ተከታዮቹም “አባት ሆይ፣ ስምህ ይቀደስ” ብለው እንዲጸልዩ አስተምሯል።​—ሉቃስ 11:2

የጥንቶቹ ክርስቲያኖች ይህን ብቃት አሟልተዋል? ሐዋርያው ጴጥሮስ፣ አምላክ ከብሔራት መካከል “ለስሙ የሚሆኑ ሰዎችን” እንደወሰደ በኢየሩሳሌም ለነበሩት ሽማግሌዎች ነግሯቸዋል። (የሐዋርያት ሥራ 15:14) ሐዋርያትም ሆኑ ሌሎች ክርስቲያኖች “የይሖዋን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናል” እያሉ ሰብከዋል። (የሐዋርያት ሥራ 2:21፤ ሮም 10:13) በተጨማሪም እነሱ በጻፏቸው መጻሕፍት ላይ መለኮታዊውን ስም ተጠቅመዋል። የአይሁዳውያንን ሕጎች አሰባስቦ የያዘውና በ300 ዓ.ም. ገደማ የተጠናቀቀው ዘ ቶሴፍታ የተባለው መጽሐፍ፣ ተቃዋሚዎች ስላቃጠሏቸው የክርስቲያን ጽሑፎች እንደሚከተለው ብሏል፦ “የወንጌላውያንንና የሚኒምን [አይሁዳውያን ክርስቲያኖች እንደሆኑ ይታመናል] መጻሕፍት ከእሳት መታደግ አልተቻለም። መጻሕፍቱን በተገኙበት ቦታ ሁሉ . . . በውስጣቸው ከሰፈረው መለኮታዊ ስም ጋር አቃጥለዋቸው ነበር።”

በዛሬው ጊዜ ብቃቱን የሚያሟሉት እነማን ናቸው? በዩናይትድ ስቴትስ በሚገኘው የክርስቶስ አብያተ ክርስቲያናት ብሔራዊ ምክር ቤት ፈቃድ የተዘጋጀው ዘ ሪቫይዝድ ስታንዳርድ ባይብል የተሰኘው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በመቅድሙ ላይ እንዲህ ይላል፦ “ከአንዱና ብቸኛ ከሆነው አምላክ መለየት የሚኖርባቸው ሌሎች አማልክት ያሉ ይመስል እርሱን በተጸውኦ ስም መጥራት ከክርስትና ዘመን በፊት በአይሁዳውያን ሃይማኖት ውስጥ የቀረ ነገር ነው፤ ለዓለም አቀፉ የክርስትና እምነትም አምላክን በተጸውኦ ስም መጥራት ተገቢ አይደለም።” በመሆኑም ይህ ትርጉም መለኮታዊውን ስም “ጌታ” በሚለው የማዕረግ ስም ተክቶታል። በቅርቡ ደግሞ ቫቲካን “በመዝሙሮችም ሆነ በጸሎቶች ላይ፣ በአራት የዕብራይስጥ ፊደላት የሚወከለውን የሐወሐ * የሚለውን የአምላክን ስም መጠቀምም ሆነ መጥራት አይገባም” የሚል መመሪያ ለጳጳሶቿ አስተላልፋለች።

በዛሬው ጊዜ የአምላክን የግል ስም የሚጠቀሙትና የሚያሳውቁት እነማን ናቸው? ሰርጌይ በአሥራዎቹ ዕድሜ ሳለ የአምላክ ስም ይሖዋ መሆኑን የሚገልጽ ፊልም ኪርጊስታን ውስጥ ተመልክቶ ነበር። ከዚያ በኋላ አሥር ለሚያህሉ ዓመታት መለኮታዊውን ስም ማንም ሲጠራው አልሰማም። ከጊዜ በኋላ በዩናይትድ ስቴትስ መኖር የጀመረ ሲሆን በአንድ ወቅት ሁለት የይሖዋ ምሥክሮች ቤቱ መጥተው የአምላክን ስም ከመጽሐፍ ቅዱስ አሳዩት። ሰርጌይ ይሖዋ በሚለው የአምላክ ስም የሚጠቀም ሃይማኖታዊ ቡድን በማግኘቱ በደስታ ፈነደቀ። የሚገርመው ዌብስተርስ ሰርድ ኒው ኢንተርናሽናል ዲክሽነሪ “ጀሆቫ ጎድ” (ይሖዋ አምላክ) የሚለውን ሐረግ “ከሁሉ በላይ የሆነና የይሖዋ ምሥክሮች የሚያመልኩት ብቸኛ አምላክ” ብሎ ፈትቶታል።

[የግርጌ ማስታወሻ]

^ አን.5 በአማርኛ መለኮታዊው ስም አብዛኛውን ጊዜ የሚጻፈው “ይሖዋ” ተብሎ ነው።