በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ገና አስደሳችና ሰላማዊ እንዲሆን የሚደረግ ጥረት

ገና አስደሳችና ሰላማዊ እንዲሆን የሚደረግ ጥረት

“በበዓል ወቅት በሚኖረው ግርግር ሳይታወቀን ልንጠመድ እንችላለን። ከበዓል ጋር ተያይዘው የሚመጡ ልማዶች ሥራ ይሆኑብናል፤ በዚያ ወቅት ፕሮግራማችን በጣም ስለሚጨናነቅ ከወዳጅ ዘመድ ጋር የምናሳልፈው ጊዜ ያጥራል። ከመጠን በላይ ስለምንወጠር አንዳንድ ጊዜ ደስታችንን ልናጣ እንችላለን።”—የቀድሞው የኦክላሆማ [ዩናይትድ ስቴትስ] አስተዳዳሪ፣ ብራድ ሄንሪ፣ ታኅሣሥ 23, 2008

የገና ወቅት ሲቃረብ አስደሳች የበዓል መንፈስ እንዲኖር የሚያደርጉ ዘፈኖች፣ ፊልሞችና የቴሌቪዥን ፕሮግራሞች ይዘጋጃሉ። ይሁንና ከዚህ በዓል ጋር በተያያዘ ትልቅ ቦታ ሊሰጠው የሚገባው ነገር ምን ይመስልሃል?

  • ኢየሱስ ክርስቶስን ማስታወስ?
  • በመስጠት ደስታ ማግኘት?
  • ችግረኞችን መርዳት?
  • ከቤተሰብ ጋር ጊዜ ማሳለፍ?
  • ሰላም እንዲሰፍን ማድረግ?

በስተ ግራ የተጠቀሱት ሄንሪ የተባሉ አስተዳዳሪ እንደገለጹት ገናን የሚያከብሩ ብዙዎቹ ሰዎች በበዓሉ ወቅት ከላይ ከተዘረዘሩት ነገሮች ውስጥ አንዱንም ማሳካት ያስቸግራቸዋል። የገና ወቅት ብዙውን ጊዜ ወከባና ውጥረት የበዛበት አልፎ ተርፎም በንግድ ላይ ያተኮረ ነው። ታዲያ በገና በዓል ወቅት ሊደረጉ እንደሚገባ የሚታሰቡትን ነገሮች ማከናወን አይቻልም ማለት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስን እንድናስታውስ፣ በልግስና እንድንሰጥ፣ ችግረኞችን እንድንረዳና ከቤተሰባችን ጋር ጊዜ እንድናሳልፍ ሁላችንንም ያበረታታናል። በተጨማሪም ሰላማዊ መሆን የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያስተምረናል። ከዚህ ቀጥሎ ያሉት ተከታታይ ርዕሶች አንዳንዶች ገናን የማያከብሩበትን ምክንያት * ከማብራራት ይልቅ ከታች ላሉት ጥያቄዎች መልስ ይሰጣሉ፦

  • አንዳንዶች ገናን ለማክበር ምክንያት መሆን ያለበት ምን እንደሆነ ይሰማቸዋል?
  • ከገና በዓል ጋር በተያያዘ የሚመኙትን ነገር ማሳካት ተፈታታኝ የሆነው ለምንድን ነው?
  • በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ከገና የተሻለ ነገር መኖሩን እንዲገነዘቡ የረዷቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ሐሳቦች የትኞቹ ናቸው?

^ စာပိုဒ်၊ 10 አንዳንድ ሰዎች ገናን ላለማክበር እንዲወስኑ ያደረጓቸውን ቅዱስ ጽሑፋዊ ምክንያቶች ለማወቅ “አንባቢያን የሚያነሱት ጥያቄ—አንዳንዶች የገና በዓልን የማያከብሩት ለምንድን ነው?” የሚለውን ላይ የሚገኘውን ርዕስ ተመልከት።