በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 1 2017 | የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብን አስደሳች ማድረግ

ምን ይመስልሃል?

አሁን ካለንበት የሥልጣኔ ዘመን አንጻር መጽሐፍ ቅዱስ ጊዜ ያለፈበት ይመስልሃል? ወይስ ምክሩ እኛ ላለንበት ዘመንም ይሠራል? መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ እንዲህ ይላል፦ “ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው፤ እንዲሁም ለማስተማር . . . ይጠቅማሉ።”2 ጢሞቴዎስ 3:16, 17

ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን አንዳንድ ጥበብ ያዘሉ ምክሮች ይዟል፤ በተጨማሪም መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ይበልጥ አስደሳች እንዲሆንልህ ማድረግ የምትችለው እንዴት እንደሆነ ይገልጻል።

 

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ያለብኝ ለምንድን ነው?

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች መጽሐፍ ቅዱስን በማንበብ ምን ጥቅም አግኝተዋል?

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ መጀመር የምችለው እንዴት ነው

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ይበልጥ ቀላልና አስደሳች እንዲሆንልህ የሚረዱህን አምስት ነጥቦች ተመልከት።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

የመጽሐፍ ቅዱስን ንባቤን አስደሳች ማድረግ የምችለው እንዴት ነው?

ቀላል ባለ ቋንቋ የተዘጋጁ ትርጉሞች፣ የቴክኖሎጂ ውጤቶችና መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የተዘጋጁ መሣሪያዎች የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህን አስደሳች ለማድረግ ይረዱሃል።

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ

መጽሐፍ ቅዱስ ሕይወቴ እንዲሻሻል የሚረዳኝ እንዴት ነው?

ይህ ጥንታዊ መጽሐፍ እጅግ ጠቃሚ የሆኑ ምክሮች ይዟል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሰዎችን ሕይወት ይለውጣል

ሞትን እፈራ ነበር!

ኢቮን ክዎሪ ‘የተፈጠርኩት ለምንድን ነው?’ የሚለው ጥያቄ ያሳስባት ነበር። የዚህን ጥያቄ መልስ ማወቋ ሕይወቷን ለውጦታል።

በእምነታቸው ምሰሏቸው

‘አምላክን በሚገባ ደስ አሰኝቷል’

የምታስተዳድረው ቤተሰብ ካለህ ወይም ትክክል እንደሆነ ለምታውቀው ነገር ጥብቅና እንድትቆም የሚጠይቅ ሁኔታ ካጋጠመህ ሄኖክ ካሳየው እምነት ምን ትምህርት ማግኘት ትችላለህ?

መጽሐፍ ቅዱስን በተሳሳተ መንገድ መረዳት ያለው አደጋ

የመጽሐፍ ቅዱስን መልእክት በተሳሳተ መንገድ መረዳት ከፍተኛ አደጋ አለው። ታዲያ መጽሐፍ ቅዱስን በትክክል መረዳት የሚቻለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

መጽሐፍ ቅዱስ፣ የሚደርስብንን መከራ ያመጣው ማን እንደሆነ ብቻ ሳይሆን መከራ የሚያበቃው እንዴት እንደሆነም ይናገራል።

በተጨማሪም . . .

መጽሐፍ ቅዱስ እርስ በርሱ ይጋጫል?

በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ያሉ የሚጋጩ የሚመስሉ ሐሳቦችንና ትርጉማቸውን በትክክል ለመረዳት የሚያስችሉ ነጥቦችን ተመልከት።