በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

በምድር ላይ ፍትሕ የሚሰፍንበት ጊዜ ይመጣ ይሆን?

ምን ብለህ ትመልሳለህ?

  • አዎ

  • አይ

  • እኔ እንጃ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ይሖዋ ለችግረኛው እንደሚሟገትና ለድሃው ፍትሕ እንደሚያሰፍን አውቃለሁ።” (መዝሙር 140:12) የአምላክ መንግሥት በምድር ላይ ፍትሕ ያሰፍናል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • አምላክ በዓለማችን ላይ ያለውን የፍትሕ መጓደል ይመለከታል፤ እንዲሁም እርምጃ ይወስዳል።—መክብብ 5:8

  • አምላክ ፍትሕን ሲያሰፍን በምድር ላይ ሰላምና ደህንነት ይሆናል።—ኢሳይያስ 32:16-18

አምላክ ያዳላል?

አንዳንዶች ምን ብለው ያምናሉ? አንዳንዶች አምላክ የተወሰኑ ዘሮችን እንደባረከ፣ ሌሎቹን ደግሞ እንደረገመ ይሰማቸዋል፤ አምላክ ሰዎችን ሁሉ በእኩል ዓይን እንደሚመለከት የሚያምኑም አሉ። አንተስ ምን ይመስልሃል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“አምላክ [አያዳላም]፤ . . . ከዚህ ይልቅ ከየትኛውም ብሔር ቢሆን እሱን የሚፈራና ትክክል የሆነውን ነገር የሚያደርግ ሰው በእሱ ዘንድ ተቀባይነት አለው።” (የሐዋርያት ሥራ 10:34, 35) በአምላክ አመለካከት ሰዎች ሁሉ እኩል ናቸው።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • መጽሐፍ ቅዱስ ለሁሉም “ብሔር፣ ነገድ፣ ቋንቋና ሕዝብ” የሚሆን “ምሥራች” ይዟል።—ራእይ 14:6