በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 143

ነቅተን በተስፋ እንጠብቃለን

ነቅተን በተስፋ እንጠብቃለን

(ሮም 8:20-25)

  1. 1. ጊዜን፣ ወቅትን ’ሚለውጠው

    አምላካችን ይሖዋ ነው።

    በጣም ቀርቧል የቁጣው ቀን፤

    ይህን እርግጠኞች ነን።

    (አዝማች)

    ነቅተን በተስፋ እንጠብቃለን፤

    ያምላክ ዓላማ ሲፈጸም

    ለማየት እንጓጓለን።

  2. 2. አምላክ ጊዜውን ወስኗል፤

    ክርስቶስም ተዘጋጅቷል።

    በቅርብ እርምጃ ይወስዳል፤

    ታላቅ ድል ይቀዳጃል።

    (አዝማች)

    ነቅተን በተስፋ እንጠብቃለን፤

    ያምላክ ዓላማ ሲፈጸም

    ለማየት እንጓጓለን።

  3. 3. ፍጥረት በጭንቅ ቢቃትትም

    እምነት አለን፤ ተስፋ ’ንቆርጥም።

    ታላቁ ያምላክ ቀን ቀርቧል፤

    ፍጥረት ነፃ ይወጣል።

    (አዝማች)

    ነቅተን በተስፋ እንጠብቃለን፤

    ያምላክ ዓላማ ሲፈጸም

    ለማየት እንጓጓለን።

(በተጨማሪም ማቴ. 25:13⁠ን እና ሉቃስ 12:36⁠ን ተመልከት።)