በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

መዝሙር 22

በሰማይ የተቋቋመው መንግሥት ይምጣልን!

በሰማይ የተቋቋመው መንግሥት ይምጣልን!

(ራእይ 11:15፤ 12:10)

  1. 1. ያለህ፣ የነበርክ፣ የምትኖር

    ይሖዋ አምላክ ሆይ፣

    ለልጅህ ሥልጣን ሰጥተሃል፤

    ዙፋኑን ተረክቧል።

    የአምላክ መንግሥት ተወልዷል፤

    በቅርቡም ምድርን ይገዛል።

    (አዝማች)

    ማዳን ያምላክ ሆኗል፤

    የሱ መንግሥት ተቋቁሟል።

    እንጸልይ ሁላችን

    ብለን “መንግሥቱ ይምጣልን!”

  2. 2. ሰይጣን ጊዜው አልቆበታል፤

    ጭንቀት፣ ችግር በዝቷል።

    ሆኖም አውቀናል እውነቱን፤

    ተስፋችን መቅረቡን።

    የአምላክ መንግሥት ተወልዷል፤

    በቅርቡም ምድርን ይገዛል።

    (አዝማች)

    ማዳን ያምላክ ሆኗል፤

    የሱ መንግሥት ተቋቁሟል።

    እንጸልይ ሁላችን

    ብለን “መንግሥቱ ይምጣልን!”

  3. 3. ከሰማይ ተሰማ ደስታ፣

    የመላ’ክት እልልታ።

    ጠላታቸው ተወርውሯል፤

    ከሰማይ ተጥሏል።

    የአምላክ መንግሥት ተወልዷል፤

    በቅርቡም ምድርን ይገዛል።

    (አዝማች)

    ማዳን ያምላክ ሆኗል፤

    የሱ መንግሥት ተቋቁሟል።

    እንጸልይ ሁላችን

    ብለን “መንግሥቱ ይምጣልን!”

(በተጨማሪም ዳን. 2:34, 35⁠ን እና 2 ቆሮ. 4:18⁠ን ተመልከት።)