በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

AspctStyle/stock.adobe.com

የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ ዘመቻ

ኢየሱስ ጦርነትን ያስወግዳል

ኢየሱስ ጦርነትን ያስወግዳል

 ኢየሱስ በምድር ላይ ሳለ ለሰዎች ታላቅ ፍቅር አሳይቷል፤ እንዲያውም ለእነሱ ሲል ሕይወቱን መሥዋዕት አድርጎ ሰጥቷል። (ማቴዎስ 20:28፤ ዮሐንስ 15:13) በቅርቡ ደግሞ፣ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ እንደመሆኑ መጠን ያለውን ሥልጣን ተጠቅሞ “ጦርነትን ከመላው ምድር ላይ ያስወግዳል።”​—መዝሙር 46:9

 መጽሐፍ ቅዱስ፣ ኢየሱስ የሚያከናውነውን ነገር የሚገልጸው እንዴት እንደሆነ ልብ በል፦

  •   “እርዳታ ለማግኘት የሚጮኸውን ድሃ፣ እንዲሁም ችግረኛውንና ረዳት የሌለውን ሁሉ ይታደጋልና። ለችግረኛውና ለድሃው ያዝናል፤ የድሆችንም ሕይወት ያድናል። ከጭቆናና ከግፍ ይታደጋቸዋል።”​—መዝሙር 72:12-14

 ኢየሱስ ላደረገልን ነገር እንዲሁም ወደፊት ለሚያደርግልን ነገር ያለንን አድናቆት ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው? በሉቃስ 22:19 ላይ ኢየሱስ ተከታዮቹን የሞቱን መታሰቢያ እንዲያከብሩ ነግሯቸዋል። በመሆኑም የይሖዋ ምሥክሮች በየዓመቱ ኢየሱስ በሞተበት ዕለት ላይ አንድ ስብሰባ ያደርጋሉ። እሁድ፣ መጋቢት 24, 2024 የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ አብረኸን እንድታከብር እንጋብዝሃለን።

በዓሉ የሚከበርበት ቦታ