በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በምድር ላይ ሰላም ሊሰፍን የሚችለው እንዴት ነው?

በምድር ላይ ሰላም ሊሰፍን የሚችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

 በምድር ላይ ሰላም ሊሰፍን የሚችለው የሰው ልጆች በሚያደርጉት ጥረት ሳይሆን በአምላክ መንግሥት አማካኝነት ነው፤ ይህ መንግሥት የሚገኘው በሰማይ ሲሆን የሚመራውም በክርስቶስ ኢየሱስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ስለዚህ አስደሳች ተስፋ የያዛቸውን ትምህርቶች ተመልከት።

  1.   አምላክ ‘ለሚወዳቸው ሰዎች በምድር ላይ ሰላም’ ለማስፈን የገባውን ቃል ለመፈጸም ሲል “ከዳር እስከ ዳር ጦርነትን ከምድር ያስወግዳል።”—መዝሙር 46:9፤ ሉቃስ 2:14

  2.   በሰማይ የሚገኘው የአምላክ መንግሥት ወደፊት መላዋን ምድር ያስተዳድራል። (ዳንኤል 7:14) መላውን ዓለም የሚገዛ እንደመሆኑ መጠን በዛሬው ጊዜ ለበርካታ ግጭቶች መንስኤ የሆነውን ዘረኝነትን ጠራርጎ ያስወግዳል።

  3.   “የሰላም ልዑል” ተብሎ የተጠራው የአምላክ መንግሥት ገዥ የሆነው ኢየሱስ ‘ፍጻሜ የሌለው ሰላም’ እንዲሰፍን ያደርጋል።—ኢሳይያስ 9:6, 7

  4.   ሰላም ማደፍረሳቸውን የሚቀጥሉ ሰዎች በአምላክ መንግሥት ሥር እንዲኖሩ አይፈቀድላቸውም፤ ምክንያቱም አምላክ “ዐመፃን የሚወዱትን . . . ነፍሱ ትጠላቸዋለች።”​—መዝሙር 11:5፤ ምሳሌ 2:22

  5.   አምላክ፣ ተገዢዎቹ በሰላም መኖር የሚችሉበትን መንገድ ያስተምራቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ፣ የአምላክ መንግሥት ተገዢዎች እንዲህ ዓይነት ትምህርት ማግኘታቸው የሚኖረውን ውጤት ሲገልጽ እንዲህ ይላል፦ “ሰይፋቸውን ቀጥቅጠው ማረሻ ጦራቸውንም ማጭድ ያደርጋሉ። ሕዝብ በሕዝብ ላይ ሰይፍ አያነሣም፤ ጦርነትንም ከእንግዲህ አይማሩም።”​—ኢሳይያስ 2:3, 4

 በዛሬው ጊዜ በዓለም ዙሪያ የሚገኙ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የይሖዋ ምሥክሮች ሰላም ፈጣሪ የሚቻልበትን መንገድ ከአምላክ ተምረዋል። (ማቴዎስ 5:9) የይሖዋ ምሥክሮች ከተለያዩ ዘሮች የተውጣጡና ከ230 በሚበልጡ አገሮች የሚኖሩ ቢሆንም የጦር መሣሪያ በማንሳት ሌላውን ሰው አይጎዱም።

 በዛሬው ጊዜ የይሖዋ ምሥክሮች የሰላምን መንገድ እየተማሩ ነው