በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በናዚ አገዛዝ ወቅት የይሖዋ ምሥክሮች ምን ደርሶባቸዋል?

በናዚ አገዛዝ ወቅት የይሖዋ ምሥክሮች ምን ደርሶባቸዋል?

 በጀርመንና ናዚዎች በተቆጣጠሯቸው ሌሎች አገሮች ውስጥ ይኖሩ ከነበሩ ወደ 35,000 የሚጠጉ የይሖዋ ምሥክሮች መካከል 1,500 የሚያህሉት፣ ናዚዎች ባደረሱት እልቂት ሞተዋል። እርግጥ ነው፣ ለአንዳንዶቹ ሞት መንስኤው ምን እንደሆነ ገና አልታወቀም። በመጣራት ላይ ያሉ ጉዳዮች በመኖራቸው ወደፊት አዳዲስ አኃዛዊና ሌሎች ዝርዝር መረጃዎች ሊወጡ ይችላሉ።

 የሞቱት እንዴት ነው?

  • ናዚዎች ይጠቀሙበት የነበረው ጊሎቲን

      የሞት ቅጣት፦ በጀርመንና ናዚዎች በተቆጣጠሯቸው አገሮች ውስጥ የሚኖሩ ወደ 400 የሚጠጉ የይሖዋ ምሥክሮች በሞት ተቀጥተዋል። አብዛኞቹ፣ ፍርድ ቤት ቀርበው የሞት ፍርድ ስለተበየነባቸው አንገታቸው ተቀልቷል። ሌሎቹ ደግሞ ፍርድ ቤት እንኳ ሳይቀርቡ በጥይት አሊያም በስቅላት ተገድለዋል።

  •   በእስር ቤት ውስጥ የነበረው አሰቃቂ ሁኔታ፦ ከ1,000 የሚበልጡ የይሖዋ ምሥክሮች በናዚ የማጎሪያ ካምፖችና እስር ቤቶች ውስጥ ሞተዋል። እነዚህ የይሖዋ ምሥክሮች እዚያ ሳሉ በደረሰባቸው ሥቃይ፣ በረሃብ፣ ለከፍተኛ ቅዝቃዜ በመጋለጣቸው፣ በመታመማቸውና ተገቢውን ሕክምና ባለማግኘታቸው አሊያም በሥራ ብዛት ሕይወታቸው አልፏል። ሁለተኛው የዓለም ጦርነት አብቅቶ ነፃ የወጡ አንዳንዶቹም እዚያ ሳሉ በደረሰባቸው ከፍተኛ እንግልት የተነሳ ከተፈቱ ብዙም ሳይቆዩ ሞተዋል።

  •   ሌሎች ምክንያቶች፦ አንዳንድ የይሖዋ ምሥክሮች ሕይወታቸውን ያጡት በመርዛማ ጭስ ታፍነው፣ ለሞት የሚዳርግ የሕክምና ሙከራ ተደርጎባቸው አሊያም የሚገድል መድኃኒት በመርፌ ተወግተው ነው።

 ሥቃይ የደረሰባቸው ለምንድን ነው?

 ናዚዎች የይሖዋ ምሥክሮችን ያሠቃዩአቸው በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን ትምህርቶች በጥብቅ በመከተላቸው ነው። የይሖዋ ምሥክሮች መጽሐፍ ቅዱስ የሚያወግዘውን ነገር እንዲያደርጉ ናዚዎች ቢጫኗቸውም ይህን ለማድረግ ፈቃደኞች አልነበሩም። እነዚህ የይሖዋ ምሥክሮች፣ ‘ከሰው ይልቅ አምላክን እንደ ገዢያቸው አድርገው ለመታዘዝ’ መርጠዋል። (የሐዋርያት ሥራ 5:29) እንዲህ ያደረጉባቸውን ሁለት አቅጣጫዎች እስቲ እንመልከት፦

  1.   ከፖለቲካ ገለልተኛ በመሆን። በዛሬው ጊዜ በሁሉም አገሮች እንደሚገኙ የይሖዋ ምሥክሮች ሁሉ በናዚ አገዛዝ ወቅት የነበሩት የይሖዋ ምሥክሮችም በፖለቲካ ጉዳዮች ገለልተኛ ነበሩ። (ዮሐንስ 18:36) በመሆኑም በሚከተሉት ነገሮች ለመካፈል ፈቃደኛ አልሆኑም፦

  2.   አምልኳቸውን በማካሄድ፦ የይሖዋ ምሥክሮች አምልኳቸውን እንዳያካሂዱ ቢከለከሉም እነሱ ግን የሚከተሉትን ነገሮች ማድረጋቸውን ቀጥለዋል፦

 ፕሮፌሰር ሮበርት ጌርቫርት ‘በሦስትኛው ራይክ (በናዚዎች አገዛዝ) ዘመን በእምነታቸው ምክንያት የተሠቃዩት’ የይሖዋ ምሥክሮች ብቻ እንደሆኑ ተናግረዋል። a በማጎሪያ ካምፖቹ ውስጥ የነበሩ ሌሎች እስረኞችም የይሖዋ ምሥክሮች ያሳዩትን ጽናት ያደንቁ ነበር። አንድ ኦስትሪያዊ እስረኛ “ወደ ጦርነት አይሄዱም። ሌላ ሰው ከሚገድሉ ይልቅ ራሳቸው ቢገደሉ ይመርጣሉ” ሲል ያስተዋለውን ተናግሯል።

 የሞቱት የት ነው?

  •   በማጎሪያ ካምፓች ውስጥ፦ ብዙዎቹ የይሖዋ ምሥክሮች የሞቱት በማጎሪያ ካምፖቹ ውስጥ ነው። እነዚህ የይሖዋ ምሥክሮች የታሰሩት እንደ ማውትሃውዘን፣ ራቨንስብሩክ፣ ቡኸንቫልድ፣ ኒደርሃገን፣ ኖየንጋሜ፣ አውሽቭትዝ፣ ዛክሰንሃውዘን፣ ዳኻውና ፍሎሰንቡርግ ባሉ ካምፖች ውስጥ ነበር። በዛክሰንሃውዘን ብቻ ወደ 200 የሚጠጉ የይሖዋ ምሥክሮች እንደሞቱ ተረጋግጧል።

  •   በእስር ቤቶች ውስጥ፦ የተወሰኑ የይሖዋ ምሥክሮች በእስር ቤቶች ውስጥ ከፍተኛ ሥቃይ ስለደረሰባቸው ሕይወታቸው አልፏል። ሌሎቹ ደግሞ የሞቱት በምርመራ ወቅት በደረሰባቸው ጉዳት ነው።

  •   በተለያዩ የግድያ ቦታዎች፦ የይሖዋ ምሥክሮች በዋነኝነት የተገደሉባቸው ቦታዎች በበርሊን-ፕልትሰንዜ፣ በብራንደንበርክ፣ በሃሌ/ዛሌ የሚገኙት እስር ቤቶች ናቸው። በተጨማሪም የይሖዋ ምሥክሮች የተገደሉባቸው ሌሎች 70 ቦታዎች እንዳሉ ታውቋል።

 ከተገደሉት መካከል

  •  ስም፦ ኸለነ ጎትሆልት

     የተገደለችበት ቦታ፦ ፕልትሰንዜ (በርሊን)

     ባለትዳርና የሁለት ልጆች እናት የሆነችው ኸለነ በተለያዩ ጊዜያት ታስራለች። በ1937 በምርመራ ወቅት በደረሰባት ከፍተኛ እንግልት ምክንያት፣ በሆዷ ውስጥ የነበረው ጽንስ ጨንግፏል። ታኅሣሥ 8, 1944 በርሊን በሚገኘው ፕልትሰንዜ እስር ቤት ጊሎቲን በተባለው መሣሪያ አንገቷ ተቆርጦ ተገደለች።

  •  ስም፦ ጌርሃርት ሊቦልድ

     የተገደለበት ቦታ፦ ብራንደንበርክ

     የ20 ዓመቱ ጌርሃርት ግንቦት 6, 1943 አንገቱ ተቀልቶ የሞተው አባቱ ከሁለት ዓመት በፊት በተገደለበት እስር ቤት ነው። ከመሞቱ በፊት ለቤተሰቦቹና ለእጮኛው በጻፈው የስንብት ደብዳቤ ላይ “ጌታ ኃይል ባይሰጠኝ ኖሮ ይህንን ማድረግ አልችልም ነበር” ብሏል።

  •  ስም፦ ሩዶልፍ አውሸነር

     የተገደለበት ቦታ፦ ሃሌ/ዛሌ

     መስከረም 22, 1944 ሩዶልፍ ሲገደል ገና 17 ዓመቱ ነበር። ለእናቱ በጻፈው የስንብት ደብዳቤ ላይ “ብዙ ወንድሞች በዚህ መንገድ ሄደዋል፤ እኔም ተመሳሳይ አቋም አለኝ” ሲል ተናግሯል።

a ሂትለርስ ሃንግማን፦ ዘ ላይፍ ኦቭ ሄይድርሽ ገጽ 105