በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

የይሖዋ ምሥክሮች ፆታዊ ጥቃትን በተመለከተ ወላጆችንም ሆነ ልጆችን ያስተምራሉ

የይሖዋ ምሥክሮች ፆታዊ ጥቃትን በተመለከተ ወላጆችንም ሆነ ልጆችን ያስተምራሉ

መጽሐፍ ቅዱስ፣ ወላጆች ልጆቻቸውን እንዲወዷቸው፣ እንዲያስተምሯቸውና ከአደጋ እንዲጠብቋቸው እንዲሁም የአምላክ ስጦታ እንደሆኑ አድርገው እንዲመለከቷቸው ይመክራል። (መዝሙር 127:3፤ ምሳሌ 1:8፤ ኤፌሶን 6:1-4) ወላጆች ልጆቻቸውን ከተለያዩ አደገኛ ሁኔታዎች ሊጠብቋቸው ይገባል፤ ከእነዚህም አንዱ ፆታዊ ጥቃት ነው።

ላለፉት በርካታ አሥርተ ዓመታት የይሖዋ ምሥክሮች፣ ቤተሰቦች እርስ በርሳቸው ጤናማ ግንኙነት እንዲኖራቸው የሚያበረታቱ ጽሑፎችንና ሌሎች መረጃዎችን አዘጋጅተው ሲያሰራጩ ቆይተዋል። በተጨማሪም ልጆችን ከፆታ ጥቃት ለመጠበቅ እንዲሁም ፆታዊ ጥቃት የሚፈጽሙ ሰዎችን በተመለከተ ለልጆች ትምህርት ለመስጠት የሚረዱ ጽሑፎችን ለወላጆች አዘጋጅተዋል። የይሖዋ ምሥክሮች ይህን ጉዳይ በተመለከተ ግልጽ የሆነ መመሪያ ሲሰጡ እንደቆዩ የሚያሳዩ አንዳንድ ርዕሶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል። እነዚህ ርዕሶች በምን ያህል ቋንቋዎች እንደተዘጋጁና ምን ያህል ቅጂዎች እንደተሰራጩ ልብ ለማለት ሞክር። a

የይሖዋ ምሥክሮች ፆታዊ ጥቃት የሚፈጽሙ ሰዎች ከሚያደርሱት ጉዳት ልጆችን ለመጠበቅ ለወላጆችም ሆነ ለልጆች ትምህርት መስጠታቸውን ይቀጥላሉ።

a የሕትመቱ ቀን የተጻፈው ከእንግሊዝኛው እትም አንጻር ነው።