በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ለታዳጊ ወጣቶች

የፍትሕ መጓደልን የሚጠላ አምላክ

የፍትሕ መጓደልን የሚጠላ አምላክ

መመሪያ፦ ይህን መልመጃ ጸጥታ በሰፈነበት ቦታ ሆነህ ሥራ። ጥቅሶቹን ስታነብ በቦታው እንዳለህ አድርገህ አስብ። ሁኔታውን በዓይነ ሕሊናህ ለመሳል እንዲሁም በታሪኩ ውስጥ የተጠቀሱት ሰዎች ሲነጋገሩ ድምፃቸውን ለመስማትና ስሜታቸውን ለመረዳት ሞክር። ታሪኩ ሕያው እንዲሆንልህ አድርግ።

ዋነኞቹ ባለታሪኮች፦ አክዓብ፣ ኤልዛቤል፣ ናቡቴ እና ኤልያስ

ታሪኩ በአጭሩ፦ አክዓብ የወይን ተክል ቦታ ለማግኘት ሲል በኤልዛቤል ገፋፊነት ሰው አስገደለ።

ሁኔታውን ለማስተዋል ሞክር።​—1 ነገሥት 21:1-26ን አንብብ።

በዚህ ዘገባ ላይ የተገለጹት አራት ባለታሪኮች ምን ዓይነት መልክ ያላቸው ይመስልሃል?

አክዓብ․․․․․

ኤልዛቤል․․․․․

ናቡቴ․․․․․

ኤልያስ․․․․․

ከቁጥር 5-7 ባለው ዘገባ ላይ ኤልዛቤልና አክዓብ የተነጋገሩት በምን ዓይነት የድምፅ ቃና ይመስልሃል?

․․․․․

ቁጥር 13 ላይ ያለው ክንውን ሲፈጽም ምን ዓይነት ሁኔታ ሊኖር እንደሚችል ግለጽ።

․․․․․

ከቁጥር 20-26 ባለው ዘገባ ላይ ኤልያስና አክዓብ በምን ዓይነት የድምፅ ቃና የተነጋገሩ ይመስልሃል?

․․․․․

ጥልቅ ምርምር አድርግ።

በቁጥር 7 እና 25 ላይ የተገለጹት የትኞቹ የኤልዛቤል መጥፎ ባሕርያት ናቸው?

․․․․․

በቁጥር 4 ላይ የተገለጹት የትኞቹ የአክዓብ መጥፎ ባሕርያት ናቸው?

․․․․․

አክዓብ የናቡቴን የወይን ተክል ቦታ ለመውሰድ ሲል እነማንን አስገድሏል? (2 ነገሥት 9:24-26⁠ን አንብብ።)

․․․․․

አክዓብ በይሖዋ ዘንድ ምን ዓይነት ስም አትርፎ ነበር? (ቁጥር 25⁠ን እና 26⁠ን በድጋሚ አንብብ። በተጨማሪም 1 ነገሥት 16:30-33⁠ን ተመልከት።)

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ያገኘኸውን ትምህርት ተግባራዊ አድርግ። ከዚህ በታች ስለሰፈሩት ሐሳቦች ምን ትምህርት እንዳገኘህ ጻፍ፦

ይሖዋ ፍትሕ የጎደላቸው ድርጊቶችን የሚመለከት ስለመሆኑ

․․․․․

ይሖዋ ግፍ ለተፈጸመባቸው ሰዎች የሚያስብ ስለመሆኑ

․․․․․

ይሖዋ የፍትሕ አምላክ መሆኑን ስላሳየበት መንገድ (ዘዳግም 32:4⁠ን አንብብ።)

․․․․․

ልትሠራበት የሚገባ ተጨማሪ ነገር፦

ዛሬ ያሉ አንዳንድ ሰዎች የኤልዛቤል ዓይነት መንፈስ የሚያንጸባርቁት እንዴት ነው? (ራእይ 2:18-21⁠ን አንብብ።)

․․․․․

የኤልያስ ዓይነት ድፍረት ማሳየት የሚያስፈልግህ ምን ዓይነት ሁኔታዎች ሲያጋጥሙህ ነው?

․․․․․

በአንተ ወይም በሌሎች ላይ የፍትሕ መጓደል ቢደርስ ስለምን ነገር እርግጠኛ መሆን ትችላለህ?

․․․․․

ከዚህ ታሪክ ውስጥ ልብህን ይበልጥ የነካው ምንድን ነው? ለምንስ?

․․․․․

ተጨማሪ ሐሳብ፦ ይህን ታሪክ በዜና መልክ ለማቅረብ ሞክር። ስለተፈጸመው ሁኔታ የሚገልጽ ዘገባ አዘጋጅ፤ ከዋነኞቹ ባለታሪኮችና በቦታው ከነበሩ የዓይን ምሥክሮች ጋር የተደረጉ ቃል ምልልሶችን በዘገባው ውስጥ አካትት።

www.ps8318.com የተባለውን ድረ ገጽ ጎብኝ

ይህን ርዕስ ወይም ሌሎች ጽሑፎችን ድረ ገጹ ላይ ማግኘት ትችላለህ