በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ምዕራፍ 11

ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህ የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህ የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው?

አንድ ትልቅ ሥራ ለመጀመር አስበህ ግን በጣም ከባድ እንደሆነ ተሰምቶህ ያውቃል? ምናልባት ሥራው ቀለል እንዲልልህ ስትል በትናንሹ ከፋፍለህ ለመሥራት ሞክረህ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስን ከማንበብ ጋር በተያያዘም ሁኔታው ተመሳሳይ ነው። ምናልባት ‘ከምን ልጀምር?’ ብለህ ታስብ ይሆናል። በዚህ ምዕራፍ ውስጥ፣ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና ማጥናት አስደሳች እንዲሆንልህ ለማድረግ የሚረዱ አንዳንድ ቀላል መንገዶችን እንመለከታለን።

1. መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረን ማንበብ ያለብን ለምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስን ወይም ‘የይሖዋን ሕግ’ አዘውትሮ የሚያነብ ሰው ደስተኛና ስኬታማ ይሆናል። (መዝሙር 1:1-3⁠ን አንብብ።) መጀመሪያ ላይ፣ በየዕለቱ ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ጥረት አድርግ። የአምላክን ቃል ይበልጥ እያወቅከው ስትሄድ ንባቡም የዚያኑ ያህል አስደሳች ይሆንልሃል።

2. ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህ የተሟላ ጥቅም ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባባችን የተሟላ ጥቅም ለማግኘት፣ የምናነበውን ነገር ቆም ብለን ልናስብበት ይገባል። ማንበብ ብቻ ሳይሆን ‘ማሰላሰልም’ አስፈላጊ ነው። (ኢያሱ 1:8 የግርጌ ማስታወሻ) መጽሐፍ ቅዱስን ስታነብ እንደሚከተሉት ያሉ ጥያቄዎችን ራስህን ጠይቅ፦ ‘ይህ ታሪክ ስለ ይሖዋ አምላክ ምን ያስተምረኛል? በሥራ ላይ ላውለው የምችለው እንዴት ነው? ይህን ሐሳብ ሌሎችን ለመርዳት ልጠቀምበት የምችለው እንዴት ነው?’

3. መጽሐፍ ቅዱስን የምታነብበት ጊዜ ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

መጽሐፍ ቅዱስን የምታነብበት ጊዜ ለማግኘት ትቸገራለህ? ብዙዎቻችን እንዲህ ያለ ችግር ያጋጥመናል። ጊዜህን ‘በተሻለ መንገድ ለመጠቀም’ ጥረት ማድረግህ በዚህ ረገድ ይረዳሃል። (ኤፌሶን 5:16) በየዕለቱ መጽሐፍ ቅዱስን የምታነብበት የተወሰነ ጊዜ መድብ። አንዳንድ ሰዎች ጠዋት ላይ መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብ ጊዜ ይመድባሉ። ሌሎች ደግሞ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ላይ ምናልባትም በምሳ እረፍታቸው ለማንበብ ይመርጣሉ። ማታ ላይ ከመተኛታቸው በፊት መጽሐፍ ቅዱስ የሚያነብቡ ሰዎችም አሉ። አንተ የምትመርጠው የትኛውን ጊዜ ነው?

ጠለቅ ያለ ጥናት

የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህን ይበልጥ አስደሳች ማድረግ የምትችለው እንዴት እንደሆነ እንመለከታለን። በተጨማሪም ከምናደርገው የመጽሐፍ ቅዱስ ውይይት የተሟላ ጥቅም ለማግኘት በደንብ መዘጋጀት የምትችለው እንዴት እንደሆነ እንማራለን።

ከዚህ በፊት በልተን የማናውቀውን ምግብ በተደጋጋሚ ስንበላው እየወደድነው ልንሄድ እንደምንችል ሁሉ መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብም በጊዜ ሂደት አስደሳች ሊሆንልን ይችላል

4. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህን አስደሳች ማድረግ የምትችለው እንዴት ነው?

መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ መጀመር ቀላል ላይሆንልህ ይችላል። ሆኖም አንድ ሰው ከዚህ በፊት በልቶት የማያውቀውን ምግብ በተደጋጋሚ ሲበላው እየወደደው ሊሄድ እንደሚችል ሁሉ አንተም ለአምላክ ቃል ‘ጉጉት እያዳበርክ’ ልትሄድ ትችላለህ። አንደኛ ጴጥሮስ 2:2 አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ማንበብህ፣ የማንበብ ጉጉት እንድታዳብር የሚረዳህ ይመስልሃል?

አንዳንዶች መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ አስደሳች እንዲሆንላቸው የረዳቸው ምን እንደሆነ ለማየት ቪዲዮውን ተመልከቱ ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦

  • ቪዲዮው ላይ የታዩት ወጣቶች ምን ተፈታታኝ ሁኔታ አጋጥሟቸዋል?

  • መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትረው ለማንበብ ያወጡትን ግብ ለማሳካት የረዳቸው ምንድን ነው?

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ንባባቸውን ይበልጥ አስደሳች ማድረግ የቻሉት እንዴት ነው?

ንባብህን ለመጀመር የሚረዱህ ምክሮች፦

  •   እምነት የሚጣልበትና ቀለል ያለ ቋንቋ የሚጠቀም የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ምረጥ። በቋንቋህ የሚገኝ ከሆነ አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስን መጠቀም ትችላለህ።

  •   በቅድሚያ ትኩረትህን የሚስቡትን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አንብብ።መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ጀምር” በተባለው ሰንጠረዥ ውስጥ አንዳንድ ጠቃሚ ሐሳቦችን ታገኛለህ።

  •   ያነበብካቸውን ክፍሎች መዝግብ። በዚህ ጽሑፍ ውስጥ የሚገኘውን “የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህን መዝግብ” የሚለውን ሰንጠረዥ ተጠቀም።

  •   JW Library®የተባለውን አፕሊኬሽን ተጠቀም። ይህን አፕሊኬሽን መጫን የሚችል ስልክ ወይም ሌላ የኤሌክትሮኒክ መሣሪያ በመጠቀም በፈለግከው ቦታ ሆነህ በተለያዩ ቋንቋዎች መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብና ማዳመጥ ትችላለህ።

  •   አዲስ ዓለም ትርጉም ላይ ያሉትን ተጨማሪ መረጃዎች ተጠቀም። ተጨማሪ መረጃዎቹ ካርታዎችን፣ ሰንጠረዦችንና የቃላት መፍቻ ይዘዋል፤ ይህም ንባብህን ይበልጥ አስደሳች ለማድረግ ይረዳሃል።

5. ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ ተዘጋጅ

መዝሙር 119:34ን አንብቡ፤ ከዚያም በሚከተለው ጥያቄ ላይ ተወያዩ፦

  • መጽሐፍ ቅዱስን ማንበብ ወይም በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለምናደርገው ውይይት መዘጋጀት ከመጀመርህ በፊት መጸለይህ ጥሩ የሆነው ለምንድን ነው?

ከምናደርገው ውይይት የተሟላ ጥቅም ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርብሃል? ምዕራፎቹን ስትዘጋጅ የሚከተሉትን ነገሮች ለማድረግ ሞክር፦

  1. ሀ. “ጠለቅ ያለ ጥናት” ከሚለው ክፍል በፊት ያሉትን አንቀጾች አንብብ።

  2. ለ. ጥቅሶቹን አውጥተህ አንብብ፤ እንዲሁም ከምትማረው ነገር ጋር የሚያያዙት እንዴት እንደሆነ ለማስተዋል ጥረት አድርግ።

  3. ሐ. ለጥያቄዎቹ መልስ በሚሆኑ ቁልፍ ቃላት ወይም ሐረጎች ላይ አስምር፤ ይህም ከአስተማሪህ ጋር በምዕራፉ ላይ ለመወያየት ይረዳሃል።

ይህን ታውቅ ነበር?

የይሖዋ ምሥክሮች የተለያዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞችን ሲጠቀሙ ቆይተዋል። አዲስ ዓለም ትርጉም ለተባለው የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም ግን ለየት ያለ ፍቅር አላቸው፤ ምክንያቱም ይህ ትርጉም ትክክለኛና ለመረዳት ቀላል ከመሆኑም ሌላ የአምላክን ስም ይጠቀማል።—የይሖዋ ምሥክሮች የራሳቸው መጽሐፍ ቅዱስ አላቸው? የሚለውን ድረ ገጻችን ላይ የወጣ ርዕስ ተመልከት።

አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ፦ “መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት በጣም አድካሚ ነው። ለእሱ የሚሆን ጊዜና ጉልበት የለኝም።”

  • አንተ ምን ትላለህ?

ማጠቃለያ

ከመጽሐፍ ቅዱስ የተሟላ ጥቅም ለማግኘት፣ የምታነብበት ጊዜ መድብ፤ የምታነበውን ነገር ለመረዳት ጸልይ፤ እንዲሁም ለምናደርገው ውይይት አስቀድመህ ተዘጋጅ።

ክለሳ

  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህ የተሟላ ጥቅም ለማግኘት ምን ማድረግ ይኖርብሃል?

  • መጽሐፍ ቅዱስን ለማንበብና ለማጥናት ለአንተ የተሻለው ጊዜ የትኛው ነው?

  • በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ለምናደርገው ውይይት አስቀድመህ መዘጋጀትህ ጥሩ የሆነው ለምንድን ነው?

ግብ

ምርምር አድርግ

ከመጽሐፍ ቅዱስ ንባብህ የተሟላ ጥቅም ለማግኘት ሊረዱህ የሚችሉ አንዳንድ ሐሳቦች የትኞቹ ናቸው?

“የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብን አስደሳች ማድረግ” (መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 1 2017)

መጽሐፍ ቅዱስን ለበርካታ ዓመታት ያነበቡ ሰዎች ምን ምክር ይሰጣሉ?

ውጤታማ የሆነ የግል ጥናት (2:06)