በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ደስተኛ ሕይወት ለመምራት የሚረዳ ጥበብ

ደስተኛ ሕይወት ለመምራት የሚረዳ ጥበብ

“በዓለም ላይ የሚታየው ክፋት፣ ጦርነት፣ ድህነት፣ በሽታና በልጆች ላይ የሚደርሰው ግፍ ቢያሳዝነኝም አሁን ተስፋ አለኝ።”—ራኒ *

ራኒ፣ የእውነተኛ ጥበብ ምንጭ ስለሆነው ስለ ፈጣሪያችን መማሯ እውነተኛ ደስታ አስገኝቶላታል። ቀጥሎ ያሉትን ርዕሶች ስታነብ፣ የፈጣሪ ትምህርቶች በሚከተሉት አቅጣጫዎች የሚጠቅሙህ እንዴት እንደሆነ ትረዳለህ፦

  • በቤተሰብ ሕይወትህ ደስተኛ ለመሆን

  • ከሌሎች ጋር በሰላም ለመኖር

  • በሕይወትህ እርካታ ለማግኘት

  • የመከራና የሞት መንስኤ ምን እንደሆነ ለመረዳት

  • የወደፊቱን ጊዜ በተስፋ ለመጠበቅ

  • ፈጣሪያችንን ለማወቅና የእሱ ወዳጅ ለመሆን

በተጨማሪም የፈጣሪ ጥበብ፣ ጥቂቶች ብቻ ሊያገኙት የሚችሉት ነገር እንዳልሆነ ትገነዘባለህ፤ የሚፈልግ ሁሉ፣ ይህን ጥበብ በነፃ ማግኘት ይችላል።

^ አን.2 በዚህ መጽሔት ውስጥ የተጠቀሱት ስሞች ተቀይረዋል።