መዝሙር 141:1-10

  • ጥበቃ ለማግኘት የቀረበ ጸሎት

    • ‘ጸሎቴ እንደ ዕጣን ይሁን’ (2)

    • የጻድቅ ወቀሳ እንደ ዘይት ነው (5)

    • ‘ክፉዎች የገዛ ወጥመዳቸው ውስጥ ይወድቃሉ’ (10)

የዳዊት ማህሌት። 141  ይሖዋ ሆይ፣ አንተን እጣራለሁ።+ እኔን ለመርዳት ፈጥነህ ድረስልኝ።+ አንተን ስጣራ በትኩረት ስማኝ።+   ጸሎቴ በአንተ ፊት እንደተዘጋጀ ዕጣን ይሁን፤+የተዘረጉት እጆቼ ምሽት ላይ እንደሚቀርብ የእህል መባ ይሁኑ።+   ይሖዋ ሆይ፣ ለአፌ ጠባቂ አድርግ፤በከንፈሮቼም በር ላይ ዘበኛ አቁም።+   ከክፉ ሰዎች ጋር መጥፎ ድርጊት እንዳልፈጽም፣ልቤ ወደ ክፉ ነገር እንዲያዘነብል አትፍቀድ፤+ጣፋጭ ከሆነው ምግባቸው አልቋደስ።   ጻድቅ ቢመታኝ፣ የታማኝ ፍቅር መግለጫ አድርጌ እቆጥረዋለሁ፤+ቢወቅሰኝ በራስ ላይ እንደሚፈስ ዘይት አድርጌ አየዋለሁ፤+ራሴም ይህን ፈጽሞ እንቢ አይልም።+ መከራ በገጠማቸው ወቅትም እንኳ መጸለዬን እቀጥላለሁ።   ፈራጆቻቸው ከገደል አፋፍ ቢጣሉም፣ሕዝቡ ለምናገራቸው ቃላት ትኩረት ይሰጣል፤ ደስ የሚያሰኙ ናቸውና።   ሰው ሲያርስና ጓል ሲከሰክስ አፈሩ እንደሚበታተን ሁሉ፣አጥንቶቻችንም በመቃብር* አፍ ላይ ተበታተኑ።   ሉዓላዊው ጌታ ይሖዋ ሆይ፣ ዓይኖቼ ግን ወደ አንተ ይመለከታሉ።+ አንተን መጠጊያዬ አድርጌአለሁ። ሕይወቴን አትውሰድ።*   ከዘረጉብኝ ወጥመድ፣ክፉ አድራጊዎች ካስቀመጡብኝ አሽክላም ጠብቀኝ። 10  ክፉዎች አንድ ላይ የገዛ ወጥመዳቸው ውስጥ ይወድቃሉ፤+እኔ ግን አንድም ነገር ሳይነካኝ አልፋለሁ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “በሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “ነፍሴንም አታፍስሳት።”