መዝሙር 55:1-23

  • ዳዊት፣ ወዳጁ በከዳው ጊዜ ያቀረበው ጸሎት

    • የቅርብ ወዳጁ ዘለፈው (12-14)

    • “ሸክምህን በይሖዋ ላይ ጣል” (22)

ለሙዚቀኞች ቡድን መሪ፤ በባለ አውታር መሣሪያዎች የሚታጀብ። ማስኪል።* የዳዊት መዝሙር። 55  አምላክ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤+ምሕረት እንድታደርግልኝ የማቀርበውንም ልመና ቸል አትበል።*+   ትኩረት ስጠኝ፤ መልስልኝም።+ ያሳሰበኝ ጉዳይ እረፍት ነስቶኛል፤+ደግሞም በጣም ተጨንቄአለሁ፤   ይህም ጠላት ከሚናገረው ቃል፣ክፉውም ሰው ከሚያሳድረው ጫና የተነሳ ነው። እነሱ በእኔ ላይ መከራ ይከምራሉና፤በቁጣም ተሞልተው በጥላቻ ዓይን ያዩኛል።+   ልቤ በውስጤ በጣም ተጨነቀ፤+የሞት ፍርሃትም ዋጠኝ።+   ፍርሃት አደረብኝ፤ ደግሞም ተንቀጠቀጥኩ፤ብርክም ያዘኝ።   እኔም እንዲህ እላለሁ፦ “ምነው እንደ ርግብ ክንፍ በኖረኝ! በርሬ ሄጄ ያለስጋት በኖርኩ ነበር።   እነሆ፣ ወደ ሩቅ ቦታ በበረርኩ፣+ በምድረ በዳም በቆየሁ ነበር።+ (ሴላ)   ከአውሎ ነፋስና ከውሽንፍር ሸሽቼመጠለያ ወደማገኝበት ቦታ ፈጥኜ በሄድኩ ነበር።”   ይሖዋ ሆይ፣ ግራ አጋባቸው፤ ዕቅዳቸውንም አጨናግፍ፤+በከተማዋ ውስጥ ዓመፅና ብጥብጥ አይቻለሁና። 10  ቅጥሮቿ ላይ ወጥተው ቀንና ሌሊት ይዞራሉ፤በውስጧም ተንኮልና መከራ አለ።+ 11  ጥፋት በመካከሏ አለ፤ጭቆናና ማታለል ከአደባባይዋ ፈጽሞ አይጠፉም።+ 12  የሚዘልፈኝ ጠላት አይደለምና፤+ቢሆንማ ኖሮ በቻልኩት ነበር። በእኔ ላይ የተነሳው ባላጋራ አይደለም፤ቢሆንማ ኖሮ ከእሱ በተሸሸግኩ ነበር። 13  ነገር ግን ይህን ያደረግከው እንደ እኔው ሰው* የሆንከው አንተ ነህ፤+በሚገባ የማውቅህ የገዛ ጓደኛዬ ነህ።+ 14  በመካከላችን የጠበቀ ወዳጅነት ነበር፤ከብዙ ሕዝብ ጋር ወደ አምላክ ቤት አብረን እንሄድ ነበር። 15  ጥፋት በድንገት ይምጣባቸው!+ በሕይወት ሳሉ ወደ መቃብር* ይውረዱ፤ክፋት በመካከላቸውና በውስጣቸው ያድራልና። 16  እኔ በበኩሌ አምላክን እጣራለሁ፤ይሖዋም ያድነኛል።+ 17  በማታ፣ በጠዋትና በቀትር እጨነቃለሁ፤ ደግሞም እቃትታለሁ፤*+እሱም ድምፄን ይሰማል።+ 18  በእኔ ላይ ጦርነት ከከፈቱ ሰዎች ይታደገኛል፤* ሰላም እንዳገኝም ያደርጋል፤እጅግ ብዙ ሰዎች በእኔ ላይ ተነስተዋልና።+ 19  ከጥንት ጀምሮ በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው አምላክ+ ይሰማል፤ምላሽም ይሰጣቸዋል።+ (ሴላ) አምላክን የማይፈሩት እነዚህ ሰዎች+ለመለወጥ ፈቃደኞች አይደሉም። 20  ከእሱ* ጋር ሰላም በነበራቸው ሰዎች ላይ ጥቃት ሰንዝሯል፤+የገባውን ቃል ኪዳን አፍርሷል።+ 21  የሚናገራቸው ቃላት ከቅቤ ይልቅ የለሰለሱ ናቸው፤+በልቡ ውስጥ ግን ጠብ አለ። ቃሎቹ ከዘይት ይልቅ የለሰለሱ ቢሆኑምእንደተመዘዘ ሰይፍ ናቸው።+ 22  ሸክምህን በይሖዋ ላይ ጣል፤+እሱም ይደግፍሃል።+ ጻድቁ እንዲወድቅ* ፈጽሞ አይፈቅድም።+ 23  አምላክ ሆይ፣ አንተ ግን ወደ ጥልቅ ጉድጓድ ታወርዳቸዋለህ።+ የደም ዕዳ ያለባቸውና አታላይ የሆኑ ሰዎች የዕድሜያቸውን ግማሽ እንኳ አይኖሩም።+ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “እርዳታ ለማግኘት ስጸልይም ራስህን አትሰውር።”
ወይም “እኩያዬ።”
ወይም “ሲኦል።” የሰው ልጆችን ሁሉ መቃብር ያመለክታል። የቃላት መፍቻውን ተመልከት።
ወይም “እጮኻለሁ።”
ቃል በቃል “ነፍሴን ይዋጃል።”
መዝ 55:13 እና 14 ላይ የተጠቀሰውን የቀድሞ ወዳጅ ያመለክታል።
ወይም “እንዲንገዳገድ፤ እንዲውተረተር።”