መዝሙር 83:1-18

  • ከጠላት ጋር በተፋጠጡበት ጊዜ የቀረበ ጸሎት

    • “አምላክ ሆይ፣ ዝም አትበል” (1)

    • ጠላቶች ነፋስ እያሽከረከረ እንደሚወስደው ኮሸሽላ ናቸው (13)

    • የአምላክ ስም ይሖዋ ነው (18)

መዝሙር። የአሳፍ+ ማህሌት። 83  አምላክ ሆይ፣ ዝም አትበል፤+አምላክ ሆይ፣ ጸጥ አትበል፤* ደግሞም ጭጭ አትበል።   እነሆ፣ ጠላቶችህ እየደነፉ ነውና፤+አንተን የሚጠሉ በእብሪት ይመላለሳሉ።*   በስውር በሕዝቦችህ ላይ የተንኮል ሴራ ይሸርባሉ፤በውድ አገልጋዮችህ* ላይ ይዶልታሉ።   “የእስራኤል ስም ተረስቶ እንዲቀር፣ኑ፣ ሕዝቡን እንደምስስ” ይላሉ።+   የጋራ ዕቅድ ይነድፋሉ፤*በአንተ ላይ ግንባር ፈጥረዋል፤*+   የኤዶምና የእስማኤላውያን ድንኳኖች፣ ሞዓብና+ አጋራውያን፣+   ጌባል፣ አሞንና+ አማሌቅ፣እንዲሁም ፍልስጤም+ ከጢሮስ ነዋሪዎች+ ጋር አበሩ።   አሦርም+ ከእነሱ ጋር ተባብሯል፤ለሎጥ ልጆችም+ድጋፍ ይሰጣሉ።* (ሴላ)   በምድያም እንዳደረግከው፣በቂሾንም ጅረት* በሲሳራና በያቢን ላይ እንዳደረግከው አድርግባቸው።+ 10  እነሱ በኤንዶር+ ተደመሰሱ፤ለምድርም ፍግ ሆኑ። 11  በመካከላቸው ያሉትን ታላላቅ ሰዎች እንደ ኦሬብና ዜብ፣+አለቆቻቸውንም* እንደ ዘባህና ጻልሙና አድርጋቸው፤+ 12  እነሱ “አምላክ የሚኖርባቸውን ቦታዎች እንውረስ” ብለዋልና። 13  አምላኬ ሆይ፣ ነፋስ እያሽከረከረ እንደሚወስደው ኮሸሽላ፣*+ነፋስ እንደሚጠርገው ገለባ አድርጋቸው። 14  ጫካን እንደሚያቃጥል እሳት፣ተራሮችን እንደሚያነድ ነበልባል፣+ 15  አንተም እንዲሁ በሞገድህ አሳዳቸው፤+በአውሎ ነፋስህም አሸብራቸው።+ 16  ይሖዋ ሆይ፣ ስምህን ይሹ ዘንድ፣ፊታቸውን በኀፍረት ሸፍን።* 17  ለዘላለም ይፈሩ፣ ይሸበሩም፤ውርደት ይከናነቡ፤ ደግሞም ይጥፉ፤ 18  ስምህ ይሖዋ የሆነው አንተ፣+አዎ፣ አንተ ብቻ በመላው ምድር ላይ ልዑል እንደሆንክ+ ሰዎች ይወቁ።

የግርጌ ማስታወሻዎች

ወይም “ዱዳ አትሁን።”
ወይም “ራሳቸውን ቀና ያደርጋሉ።”
ቃል በቃል “በሸሸግካቸው።”
ወይም “ቃል ኪዳን ተጋብተዋል።”
ቃል በቃል “በአንድ ልብ ይማከራሉ።”
ቃል በቃል “ክንድ ሆኑ።”
ወይም “ደረቅ ወንዝ።”
ወይም “መሪዎቻቸውንም።”
ወይም “አረም።”
ቃል በቃል “ሙላው።”