መዝሙር 34:1-22

  • ይሖዋ አገልጋዮቹን ይታደጋል

    • “በኅብረት ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ” (3)

    • የይሖዋ መልአክ ይጠብቃል (7)

    • “ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም” (8)

    • ‘ከአጥንቶቹ አንዳቸውም አልተሰበሩም’ (20)

ዳዊት በአቢሜሌክ* ፊት አእምሮውን የሳተ መስሎ በመቅረቡ+ አባሮ ባስወጣው ጊዜ የዘመረው መዝሙር። א [አሌፍ] 34  ይሖዋን ሁልጊዜ አወድሰዋለሁ፤ውዳሴው ምንጊዜም ከአፌ አይለይም። ב [ቤት]   በይሖዋ እኩራራለሁ፤*+የዋሆች ሰምተው ሐሴት ያደርጋሉ። ג [ጊሜል]   ይሖዋን ከእኔ ጋር አወድሱት፤+በኅብረት ስሙን ከፍ ከፍ እናድርግ። ד [ዳሌት]   ይሖዋን ጠየቅኩት፤ እሱም መለሰልኝ።+ ከምፈራው ነገር ሁሉ ታደገኝ።+ ה []   እሱን ተስፋ ያደረጉ በደስታ ፈኩ፤ፊታቸው ፈጽሞ ለኀፍረት አይዳረግም። ז [ዛየን]   ይህ ችግረኛ ተጣራ፤ ይሖዋም ሰማው። ከጭንቀቱ ሁሉ ገላገለው።+ ח [ኼት]   የይሖዋ መልአክ አምላክን በሚፈሩ ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፤+ደግሞም ይታደጋቸዋል።+ ט [ቴት]   ይሖዋ ጥሩ መሆኑን ቅመሱ፤ እዩም፤+እሱን መጠጊያ የሚያደርግ ሰው ደስተኛ ነው። י [ዮድ]   ቅዱሳን አገልጋዮቹ ሁሉ፣ ይሖዋን ፍሩ፤እሱን የሚፈሩ የሚያጡት ነገር የለምና።+ כ [ካፍ] 10  ብርቱ ደቦል አንበሶች እንኳ የሚበሉት አጥተው ይራባሉ፤ይሖዋን የሚሹ ግን መልካም ነገር አይጎድልባቸውም።+ ל [ላሜድ] 11  ልጆቼ ሆይ፣ ኑ፣ አዳምጡኝ፤ይሖዋን መፍራት አስተምራችኋለሁ።+ מ [ሜም] 12  ከእናንተ መካከል በሕይወት የሚደሰት፣ብዙ መልካም ዘመን ማየት የሚወድስ ማን ነው?+ נ [ኑን] 13  እንግዲያው ምላስህን ከክፉ ነገር ጠብቅ፤+በከንፈሮችህም ከማታለል ተቆጠብ።+ ס [ሳሜኽ] 14  ክፉ ከሆነ ነገር ራቅ፤ መልካም የሆነውንም አድርግ፤+ሰላምን ፈልግ፤ ተከተለውም።+ ע [አይን] 15  የይሖዋ ዓይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉ፤+ጆሮዎቹም እርዳታ ለማግኘት የሚያሰሙትን ጩኸት ይሰማሉ።+ פ [] 16  ሆኖም የክፉዎችን መታሰቢያ ሁሉ ከምድር ለማጥፋት፣የይሖዋ ፊት በእነሱ ላይ ነው።+ צ [ጻዴ] 17  ጻድቃን ጮኹ፤ ይሖዋም ሰማቸው፤+ከጭንቀታቸውም ሁሉ ገላገላቸው።+ ק [ኮፍ] 18  ይሖዋ ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፤+መንፈሳቸው የተደቆሰባቸውንም* ያድናል።+ ר [ረሽ] 19  የጻድቅ ሰው መከራ* ብዙ ነው፤+ይሖዋ ግን ከመከራው ሁሉ ይታደገዋል።+ ש [ሺን] 20  አጥንቶቹን ሁሉ ይጠብቃል፤አንዳቸውም ቢሆኑ አልተሰበሩም።+ ת [ታው] 21  ክፉ ሰው በአደጋ ይሞታል፤ጻድቁን የሚጠሉ ሰዎችም ይፈረድባቸዋል። 22  ይሖዋ የአገልጋዮቹን ሕይወት* ይዋጃል፤እሱን መጠጊያ የሚያደርጉ ሁሉ አይፈረድባቸውም።+

የግርጌ ማስታወሻዎች

ይህ የንጉሥ አንኩስ የማዕረግ ስም እንደሆነ ይታመናል።
ወይም “ነፍሴ በይሖዋ ትኩራራለች።”
ወይም “ተስፋ የቆረጡትንም።”
ወይም “ጭንቀት።”
ወይም “ነፍስ።”